Blog

የተዘናጋንበት የሚመስለው የኤች አይቪ ጉዳይ ….

ባለፉት አመታት እንደ ሀገር ኤች አይቪ ኤድስን በመከላከልና በመቆጣጠር ረገድ የተመዘገበው ውጤት በመንግስትና በህብረተሰቡ ውስጥ መዘናጋትን በመፍጠሩ የበሽታው ስርጭት አሳሳቢ ደረጃ ላይ መድረሱ ተገለፀ። አለማችን ከሁለተኛው የአለም ጦርነት መገባደድ በኋላ ትልቅ ስጋቶች ተጋርጠውበታል። የመጀመሪያው በሰው ሰራሽና የተፈጥሮ ምክንያት የሚጠፋው የሰው ልጅ ቁጥር መብዛት ፣ በተለያዩ ሀገራት የሚፈፀሙ የሽብር አደጋዎችና መድሀኒት የለሽ በሽታዎች መከሰት በብዛት አምራች […]

በንፁ የመጠጥ ውሃ የበለፀገ ዞን ለመፍጠር ተግተን እንሰራለን

ውሃ በዓለማችን ላይ በእጅጉ ለሕይወት አስፈላጊ ከሆኑት ንጥረነገሮች ዋነኛው ነው። ውሃ ለሰው ልጅ እጅግ ጠቃሚ ነው። የሰውነታችንን ሁለት ሶስተኛ ክብደትንም ይይዛል፣ ሰውነታችን ውስጥ ያሉ ንጥረ ነገሮችና አላሰፈላጊ ቆሻሻዎችን ያጓጉዛል፣ የሰውነታችንን ሙቀት ይቆጣጠራል፣ ሰውነታችን እንዲለሰልስና መገጣጠሚያዎቻችን ላይ የሚፈጠርን መጎርበጥ እንዲቀንስ ያደርጋል፣ ሰውነታችን ውስጥ የሚካሄድ የኬሚካል ውህደትን ያግዛል። ሰዎች ተፈጥሮአዊ እንቅስቃሴዎችን ሲያደርጉ በላብ፣ በሽንትና በትንፋሽ በኩል ሰውነታቸው […]

የጤና መድህን አባልነት ለጋራ ብልፅግና …..

በቤንች ሸኮ ዞን በ2016 ዓ.ም የማህበረሰብ አቀፍ ጤና መድህን አጠቃላይ አባላት ምጣኔ 67 ሺህ 705 ይህም በመቶኛ 63% ነው። ማህበረሰብ አቀፍ ጤና መድህን ትርፍን መሰረት የማያደርግ የጤና መድህን ዓይነት ሆኖ በአባልነት የሚያቅፋቸው መደበኛ ባልሆነ ክፍለ ኢኮኖሚ ተሰማርተው የሚገኙ እና በአብዛኛው በኢኮኖሚና በማህበራዊ እንቅስቃሴያቸው ከፍተኛ ቁርኝት እንዲሁም ትውውቅ ያላቸውን የህብረተሰብ ክፍል የያዘ ነው። ሁሉን አቀፍ የጤና […]

ቤንች ሸኮ የሙዝ ደን

በቤንች ሸኮ ዞን  ከፍራፍሬዎች ያንበሳውን ድርሻ በመያዝ ግንባር ቀደም የሆነውና ከበቆሎ ምርትና ቡና ምርት በተከታይነት 3ኛ ደረጃን የተጎናፀፈው የሙዝ ተክላችን የሙዝ ተክል ለመጀመርያ ጊዜ ወደ ሀገራችን የገባው በ1946 ዓ.ም ከኬንያ በሚሽነሪዎችና በቤተክርስቲያን ሰዎች አማካኝነተ እንደሆነ ይነገራል፡፡ ይህ የሙዝ ዝርያ አሁም ካለው ሙዝ ሲነፃጸር ቁመቱ እና ፍሬው አጭር የሆነ የኬንያ ሙዝ የሚባል ነበር፡፡ ይህ የኬንያ ሙዝ […]

የቤንች ሸኮ ዞን ምክር ቤት 4ኛ ዙር 11ኛ ዓመት 8ኛ መደበኛ ጉባኤ በሚዛን አማን መካሄድ ጀምሯል።

ሚዛን አማን ፣ የካቲት 25/2016 ምክር ቤቱ በ2 ቀናት ውሎ የምክር ቤትና የአስፈጻሚ ተቋማትን የመጀመሪያ ግማሽ ዓመት አፈጻጸም ጨምሮ በ5 አጀንዳዎች ላይ የሚመክር ሲሆን በጉባኤው ማጠቃለያ የአመራር ሹመት እንደሚካሄድም ታውቋል። የቤንች ሸኮ ዞን ምክር ቤት ዋና አፈ ጉባኤ ክቡር አቶ ጌዲዮን ኮስታብ ጉባኤውን በንግግር ሲከፍቱ እንደተናገሩት ምክር ቤቶች የህዝብ ሉአላዊነት መገለጫ ናቸው ብለዋል። በዚህም የዞኑ […]

የሚዛን አማን አውሮፕላን ማረፊያ ግንባታ በፍጥነት እንዲጠናቀቅ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በቅንጅት እየተሰራ ነው። አቶ ሀብታሙ ካፍቲን

የቤንች ሸኮ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ሀብታሙ ካፍቲን የሚዛን አማን ከተማ አየር ማረፊያ ግንባታ በተመለከተ ለሚዲያዎች መግለጫ ሰጥተዋል። በመግለጫቸውም ለሚዛን አማን አውሮፕላን ማረፊያ ግንባታ ከሚያስፈልገው መሬት ውስጥ 1 መቶ 27 ሄክታሩ የካሳ ክፍያ ተጠናቋል። የአውሮፕላን ማረፊያው ለዞናችን ብሎም ለሀገሪቱ ካለው ዘርፈ ብዙ ጠቀሜታ አንፃር የዞኑ መንግስት በትኩረት እየሰራ ነው ብለዋል። ግንባታው በፍጥነት እንዲጠናቀቅ ቦታውን ከይገባኛል […]

ርዕሳነ መስተዳድሮች ጠ/ሚ ዐቢይ (ዶ/ር) የፋኦን አግሪኮላ ሜዳልያ በመሸለማቸው የእንኳን ደስ አላችሁ መልዕክት አስተላለፉ

የክልል ርዕሳነ መስተዳድሮች ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የከበረውን የፋኦ አግሪኮላ ሜዳልያ በመሸለማቸው የእንኳን ደስ አላችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰው ባስተላለፉት መልዕክት÷ ሽልማቱ ኢትዮጵያን በዓለም አደባባይ ከፍ የሚያደርግ እና የላቀ ገፅታዋን የሚያሳድግ በመሆኑ ላበረከቱት አስተዋጽዖም እናመሠግናለን ብለዋል፡፡ በተመሳሳይ የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልላዊ መንግስት ርዕሰ መስተዳድር ነጋሽ ዋጌሾ (ዶ/ር ኢ/ር) […]

ርዕሰ መስተዳድር ዶ/ር ኢንጂነር ነጋሽ ዋጌሾ ከኢፌዲሪ መከላከያ ሠራዊት ማዕከላዊ ዳሎል ዕዝ ከፍተኛ አመራሮች ጋር ዉይይት አደረጉ

የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል መንግስትና የፌደራል ከፍተኛ የፀጥታ አመራሮች በክልሉ የተመዘገበውን ሠላም ወደላቀ ደረጃ ማሸጋገር በሚቻልበት ሁኔታ ላይ ነዉ ዉይይቱ ያተኮረዉ። በዉይይቱ በክልሉ የተመዘገበውን ሠላም ወደ ላቀ ደረጃ ለማሸጋገር በጋራ መስራት በሚቻልባቸዉ ጉዳዮች ላይ እና ሠላሙን አስጠብቆ ለመቀጠልም የቀጣይ የትኩረት አቅጣጫዎች ላይ ምክክር ተደርጓል: በክልሉ ያለው የሰላም ሁኔታ ከ አስተማማኝ እየሆነ መምጣቱንና ይህም የፀጥታ […]

የቤንች ሸኮ ዞን መስተዳድር ምክር ቤት የ2016 የመጀመሪያ ግማሽ ዓመት ዕቅድ አፈፃፀም ግምገማ እየተካሄደ ይገኛል።

ሚዛን አማን ፣ ጥር 20/2016 መስተዳድር ምክር ቤቱ ለ3 ቀናት በሚቆየው መድረኩ የዞን ማዕከል የአስፈጻሚ ተቋማትን የግማሽ ዓመት ዕቅድ አፈጻጸም የሚገመግም ይሆናል። የቤንች ሸኮ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ሀብታሙ ካፍትን መድረኩን በንግግር ሲከፍቱ እንደተናገሩት አመራርነት ዕድል ሳይሆን ህዝብን በታማኝነትና በቅንነት የማገልገል የሚሰጥ ትልቅ ኃላፊነት ነው ብለዋል። ዛሬ ላይ ያደጉና የበለፀጉ ሀገራት ትልቁ ሚስጥር አመራሩ የተሰጠውን […]

ከ8 ሺ በላይ አርሶ አደሮችን ተጠቃሚ የሚያደርግ የካሹ መስኖ ግድብ ግንባታ ጥናት ዙሪያ ከባለድርሻ አካላት ጋር የምክክር መድረክ ተካሄደ።

በቤንች ሸኮ ዞን ሼይ ቤንችና ደቡብ ቤንች ወረዳ መሀል የካሹ ወንዝ ላይ የሚገነባው የመስኖ ግድብ ጥናት አስመልክቶ ከሁለቱ ወረዳ የሚመለከታቸው አካላት ጋር የምምክር መድረክ ተካሄዷል። በኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ዲዛይንና ሱፐርቪዥን ስራዎች ኮርፖሬሽን አማካኝነት የሚጠናው ይህ ፕሮጀክት በአጭር ጊዜ ተጠንቶ እንዲጠናቀቅ ያስችል ዘንድ አጠቃላይ የጥናት ስራውን አስመልክቶ ሰነድ ቀርቦ ውይይት ተደርጎበታል። በውይይት መድረኩ ላይ ተገኝተው ንግግር ያደረጉት […]

Back To Top