Author: admin

የመሠረተ ልማት ጥያቄ ችግሮች ን ለመፍታት ትኩረት ተሰጥቶት እንዲሰራ የቤንች ሸኮ ዞን ዋና አስተዳዳሪ ክቡር አቶ ቀበሌ መንገሻ ጠየቁ።

የመሠረተ ልማት ጥያቄ ችግሮች ን ለመፍታት ትኩረት ተሰጥቶት እንዲሰራ የቤንች ሸኮ ዞን ዋና አስተዳዳሪ ክቡር አቶ ቀበሌ መንገሻ ጠየቁ። የኢፌዴሪ ህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት በቤንች ሸኮ ዞን የክልልና የህዝብ ተወካዮች በተገኙበት ውይይት አካሂደዋል። የደቡብ ምዕራብ ህዝቦች ክልላዊ መንግስት ከተደራጁ ጀምሮ በክልሉ ሠላም ፣ ልማትና ወንድማማችነት ላይ በሁሎም ዞኖችና ወረዳዎች ሲሰራ መቆየቱን የኢፌዴሪ ህዝብ ተወካዮች […]

“ደም በመለገስ በደም መፍሰስ ሕይወታቸውን የሚያጡ ወገኖችን መታደግ ይገባል” አቶ ሳሙኤል አሰፋ

“ደም በመለገስ በደም መፍሰስ ሕይወታቸውን የሚያጡ ወገኖችን መታደግ ይገባል” አቶ ሳሙኤል አሰፋ በቤንች ሸኮ ዞን ሴቶች ህፃናት ወጣቶችና ማህበራዊ ጉዳይ መምሪያ አስተባባሪነት በክረምት ወጣቶች በጎ አድራጎት በሚዛን አማን ከተማ የደም ልገሳ መርሃ ግብር ተካሄዷል። በመርሀ ግብሩ ላይ የተገኙት የቤንች ሸኮ ዞን ምክትል አስተዳዳሪና የፋይናንስና ኢኮኖሚ ልማት መምሪያ ሀላፊ አቶ ሳሙኤል አሰፋ ደም በሰጡበት ጊዜ ደም […]

የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት በሚዛን ቴፒ ዩኒቨርስቲ ቲቺንግ ሆስፒታል በመገኘት የሆስፒታሉን አጠቃላይ የስራ እንቅስቃሴና ግንባታዎችን ተዘዋውረው ጎበኙ።

የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት በሚዛን ቴፒ ዩኒቨርስቲ ቲቺንግ ሆስፒታል በመገኘት የሆስፒታሉን አጠቃላይ የስራ እንቅስቃሴና ግንባታዎችን ተዘዋውረው ጎበኙ። ሚዛን አማን ፣ ነሀሴ 21/2015 አባላቱ በመጀመሪያ ቀን በከሰዓት ውሎአቸው በሆስፒታሉ በመገኘት አጠቃላይ ስራዎችንና የጤና ኮሌጅ ግንባታዎችን ጎብኝተዋል። የሚዛን ቴፒ ዩኒቨርስቲ ቲቺንግ ሆስፒታል በቀድሞ የሚዛን አማን አጠቃላይ ሆስፒታል በሚል በ1972 ዓመተ ምህረት አካባቢ ለ60ሺ ህዝብ አገልግሎት ይሰጣል […]

ትምህርት ቤቶችን ምቹ የመማሪያ አካባቢና በግብዓት ማጠናከር የተማሪን ውጤትና ስነ-ምግባር በማሻሻል ረገድ የሚያበረክተው ሚና የጎላ መሆኑ ተገለጸ፡፡

ትምህርት ቤቶችን ምቹ የመማሪያ አካባቢና በግብዓት ማጠናከር የተማሪን ውጤትና ስነ-ምግባር በማሻሻል ረገድ የሚያበረክተው ሚና የጎላ መሆኑ ተገለጸ፡፡ ነሐሴ 20/2015 ሚዛን አማን፡ የቤንች ሸኮ ዞን ትምህርት መምሪያ በ2016 በጀት ዓመት በትምህርት ዝግጅት ምዕራፍ እየተከናወኑ ያሉ ተግባራት ዙሪያ የሚመለከታቸዉን ባለድርሻ አካላት በማሳተፍ በሚዛን አማን እየገመገመ ነው፡፡ የቤንች ሸኮ ዞን ትምህርት መምሪያ ኃላፊ አቶ ግዛው ኃይሌ እንደገለጹት የ2016 […]

ኢትዮጵያ በሴቶች ማራቶን ውድድር የወርቅ እና የብር ሜዳሊያ አገኘች

ኢትዮጵያ በሴቶች ማራቶን ውድድር የወርቅ እና የብር ሜዳሊያ አገኘች በ19ኛው የዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና በሴቶች ማራቶን ውድድር አትሌት አማኔ በሪሶ የወርቅ እና አትሌት ጎይቲቶም ገብረስላሴ የብር ሜዳሊያ ለኢትዮጵያ አስገኝተዋል። እንኳን ደስ አለን!

ኢትዮጵያ የብሪክስ አባል መሆኗ ትልቅ ዲፕሎማሲያዊ ድል ነዉ::የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልላዊ መንግስት

ኢትዮጵያ የብሪክስ አባል መሆኗ ትልቅ ዲፕሎማሲያዊ ድል ነዉ::የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልላዊ መንግስት የመግለጫዉ መሉ ቃል ቀጥሎ ቀርቧል። ” የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልላዊ መንግስት ሀገራችን ኢትዮጵያ የብሪክስ አባልነት ጥያቄዋ ተቀባይነት በማግኘቱ ለመላዉ ኢትዮጵያዊን እንኳን ደስ አለችሁ!እንኳን ደስ አለን ለማለት ይወዳል። ሀገራችን የብሪክስ አባልነት ጥያቄ ካቀረቡ 40 በላይ ሀገራት ውስጥ መስፈርቶችን አሟልታ ጥያቄዋ ተቀባይነት ማግኘቱ […]

የገበታ ለትውልድ ፕሮጀክት አካል የሆነው የደንቢ የመስህ ፕሮጀክት 372.5 ሄክታር ይዞታን የመከለልና ጋይድ ማፕ የማዘጋጀት ስራ እየተሰራ ነው፦ አቶ ጌታቸው ኮይካ

የገበታ ለትውልድ ፕሮጀክት አካል የሆነው የደንቢ የመስህ ፕሮጀክት 372.5 ሄክታር ይዞታን የመከለልና ጋይድ ማፕ የማዘጋጀት ስራ እየተሰራ ነው፦ አቶ ጌታቸው ኮይካ ሚዛን አማን ፣ ነሀሴ 19/2015 ዞኑ የቱሪዝም ፣ የኮንፍረንስ ቱሪዝም ፣ የንግድና የኢንቨስትመንት ማዕከል ከመሆኑ ጋር ተያይዞ መስህቡ መገንባት ቅልቅ ፋይዳ ያለው ነው ብለዋል። የቤንች ሸኮ ዞን ባህል ቱሪዝምና ስፖርት መምሪያ ኃላፊ አቶ ጌታቸው […]

ለዜጎች የሥራ ዕድል ከመፍጠር ባለፍ ስራ ፈጣሪ መሆን እንዲችሉ ዘርፈ ብዙ ስራዎችን እየሠራ እንደሚገኝ የቤንች ሸኮ ዞን የስራ ክህሎት ኢንተርፕራይዞችና ኢንዱስትሪ ልማት መምሪያ አሳወቀ።

ለዜጎች የሥራ ዕድል ከመፍጠር ባለፍ ስራ ፈጣሪ መሆን እንዲችሉ ዘርፈ ብዙ ስራዎችን እየሠራ እንደሚገኝ የቤንች ሸኮ ዞን የስራ ክህሎት ኢንተርፕራይዞችና ኢንዱስትሪ ልማት መምሪያ አሳወቀ። ሚዛን-አማን፦ነሐሴ 18/2015 ዓ.ም የቤንች ሸኮ ዞን የስራ ክህሎት ኢንተርፕራይዞችና ኢንዱስትሪ ልማት መምሪያ የ2015 ዓ.ም አፈፃፀም ፣የ2016 መሪ ዕቅድ እና የስራ ፈላጊ ወጣቶች ልየታ የንቅናቄ መድረክ ተካሄዷል። በንቅናቄው መድረክ ተገኝተው መልዕክት ያስተላለፉት […]

ኢትዮጵያ ብሪክስን መቀላቀሏ ትልቅ እድል ነው፡- ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)

ኢትዮጵያ ብሪክስን መቀላቀሏ ትልቅ እድል ነው፡- ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የብሪክስ መሪዎች በ15ኛው የቡድኑ ጉባኤ ኢትዮጵያን አዲስ አባል እንድትሆን ድጋፍ ማድረጋቸው እና መወሰናቸው ለኢትዮጵያ መልካም አጋጣሚ እና ትልቅ እድል መሆኑን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ገለፁ። ጠቅላይ ሚኒሰትሩ ኢትዮጵያ ብሪክስን መቀላቀሏን ተክትሎ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት መልእክት፤ “ኢትዮጵያ ሁሉን ያሳተፈ እና የበለፀገ ዓለም አቀፍ […]

በክልሉ አንድ የተቀናጀ እና የሚናበብ የኮሙኒኬሽን ቤተሰብ በመፍጠር የተግባቦት ሥራን ውጤታማ ማድረግ ይቻላል:-አቶ የሺዋስ ዓለሙ

በክልሉ አንድ የተቀናጀ እና የሚናበብ የኮሙኒኬሽን ቤተሰብ በመፍጠር የተግባቦት ሥራን ውጤታማ ማድረግ ይቻላል:-አቶ የሺዋስ ዓለሙ የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልላዊ መንግስት የመንግሥት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ ውጤታማ ተግባቦት የመፍጠር አስፈላጊነት በሚል መርህ ሃሳብ ለሚዲያ እና ኮሙዩኒኬሽን አመራሮችና ባለሙያዎች የተዘጋጀ የፓናል ውይይት መድረክ ተጀምሯል ፡፡ በምክክር መድረኩ የክልሉ የመንግሥት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ ኃላፊ አቶ የሺዋስ ዓለሙ እንደገለፁት […]

Back To Top