ኢትዮጵያ ብሪክስን መቀላቀሏ ትልቅ እድል ነው፡- ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)
የብሪክስ መሪዎች በ15ኛው የቡድኑ ጉባኤ ኢትዮጵያን አዲስ አባል እንድትሆን ድጋፍ ማድረጋቸው እና መወሰናቸው ለኢትዮጵያ መልካም አጋጣሚ እና ትልቅ እድል መሆኑን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ገለፁ።
![](https://benchshekozonecom.gov.et/wp-content/uploads/2023/08/download-2.png)
ጠቅላይ ሚኒሰትሩ ኢትዮጵያ ብሪክስን መቀላቀሏን ተክትሎ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት መልእክት፤ “ኢትዮጵያ ሁሉን ያሳተፈ እና የበለፀገ ዓለም አቀፍ ሥርዓት እንዲኖር ከሁሉም ጋር ለመተባበር ዝግጁ ነች” ብለዋል።