“ደም በመለገስ በደም መፍሰስ ሕይወታቸውን የሚያጡ ወገኖችን መታደግ ይገባል” አቶ ሳሙኤል አሰፋ

“ደም በመለገስ በደም መፍሰስ ሕይወታቸውን የሚያጡ ወገኖችን መታደግ ይገባል” አቶ ሳሙኤል አሰፋ

በቤንች ሸኮ ዞን ሴቶች ህፃናት ወጣቶችና ማህበራዊ ጉዳይ መምሪያ አስተባባሪነት በክረምት ወጣቶች በጎ አድራጎት በሚዛን አማን ከተማ የደም ልገሳ መርሃ ግብር ተካሄዷል።

በመርሀ ግብሩ ላይ የተገኙት የቤንች ሸኮ ዞን ምክትል አስተዳዳሪና የፋይናንስና ኢኮኖሚ ልማት መምሪያ ሀላፊ አቶ ሳሙኤል አሰፋ ደም በሰጡበት ጊዜ ደም በመለገስ በደም መፍሰስ ሕይወታቸውን የሚያጡ ወገኖችን መታደግ ይገባል ብለዋል።

በዞኑ በሁሉም መዋቅሮች በዘንድሮው የክረምት ወራት በጎ አድራጎት ስራ ተጠናክሮ ቀጥሏል ብለዋል።

ትናት በሚዛን አማን ከተማ በተደረገው የደም ልገሳ መርሐ ግብር ላይ 20 ዩኒት ደም መሰብሰብ ተችሏል። በተመሳሳይ በሁሉም መዋቅሮች የደም ልገሳ መርሃ ግብር ተከናውኗል።

ድረ ገጽ፦ www.benchshekozonecom.gov.et
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/benchshekozonepublicrelationoffice
ዩትዩብ፦ https://youtube.com/@BenchShekoZoneGovernmentCommun?feature=share8
ቴሌግራም፦ https://t.me/bszgca
ትዊተር፦ https://twitter.com/BenchGov?t=V1DGL3YnPHirGEiTq-jh2A&s=09
ኢንስታግራም፦ https://instagram.com/benchshekozonepr?utm_source=qr&igshid=MzNlNGNkZWQ4Mg%3D%3D
ቲክቶክ፦ tiktok.com/@benchshekozonegov
በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Back To Top