የጤና መድህን አባልነት ለጋራ ብልፅግና …..

በቤንች ሸኮ ዞን በ2016 ዓ.ም የማህበረሰብ አቀፍ ጤና መድህን አጠቃላይ አባላት ምጣኔ 67 ሺህ 705 ይህም በመቶኛ 63% ነው።

ማህበረሰብ አቀፍ ጤና መድህን ትርፍን መሰረት የማያደርግ የጤና መድህን ዓይነት ሆኖ በአባልነት የሚያቅፋቸው መደበኛ ባልሆነ ክፍለ ኢኮኖሚ ተሰማርተው የሚገኙ እና በአብዛኛው በኢኮኖሚና በማህበራዊ እንቅስቃሴያቸው ከፍተኛ ቁርኝት እንዲሁም ትውውቅ ያላቸውን የህብረተሰብ ክፍል የያዘ ነው።

ሁሉን አቀፍ የጤና መድህን ተደራሽ ለማድረግ የጤና አገልግሎት ጥራትን ለማሳደግ እና የጤና እንክብካቤ በማድረግ ገንዘብ የማገኛ ሲስተም ለማጠናከር የተዘረጋ የጤና መድህን ስርዓትን በሀገራችን ከተጀመረ አስረኛ ዓመቱን አስቆጥሯል።

አርሶ አደሩንና አርብቶ አደሩን እንዲሁም በጥቃቅንና አነስተኛ የተደራጁትን ተጠቃሚ ለማድረግ ታሳቢ ያደረገ ፕሮግራም ነው።

እንደ ሀገር የጤና አገልግሎት ለማረጋገጥ ሲባል የተለያዩ ሪፎርሞችን በጤናው ሴክተር እያካሄደ ይገኛል ፡፡

ከሪፎርሞቹም አንደኛው የጤና አገልግሎት ክፍያ ስርዓቱን ለዜጎች ፍትሃዊ ተጠቃሚነት የማረጋገጥ ሁኔታ በመሆን አግባብን በመቅረፅ ስለነበረ የዛሬ አስራ አንድ አመት የቅድመ ክፍያ የጤና መድህን ስርዓት እንደሀገር ተዘርግቷል፡፡

የቤንች ሸኮ ዞን ጤና መምሪያ ኃላፊ አቶ ኤሊያስ ምናሴ እንዳሉት የማህበረሰብ አቀፍ የጤና መድህን ካለው ዘርፈ ብዙ ጠቀሜታ አንፃር በዞኑ ያሉ ሁሉም መዋቅር ላይ የተጀመረ መሆኑን ገልፀዋል ።

ከክልል ጀምሮ እስከ ታችኛው መዋቅር የተለያዩ የቅድመ ዝግጅት ሥራዎች በመስራት ከዚያም አንዱ ራሱን የቻለ ንቅናቄ መድረኮችን በማድረግ በ2016 ዓ.ም ሥራው ውስጥ መገባቱን ኃላፊው ገልፀዋል።

በዞኑ በ2015 ዓ.ም ከነበረበት 52 ከመቶ በዚህ ዓመት ወደ 63 ከመቶ ማድረስ ተችሏል ብለዋል።

በማህበረሰብ ጤና መድህን ላይ ከመድኃኒት አቅርቦትና ከአገልግሎት አሰጣጥ አንፃር ከተጠቃሚዎች የሚመጣውን ቅሬታ ለመፍታት
የኮሚኒቲ ፋርማሲ የማዘጋጀትና ከጤና ባለሙያዎች ጋር በአገልግሎት አሰጣጥ የሚነሱ ችግሮችን ለመፍታት ተከታታይነት ያለው ውይይት እየተደረገ መሆኑን ገልፀዋል።

አቶ ሄኖክ አባጅፋር የቤንች ሸኮ ዞን ጤና መምሪያ የማህበረሰብ ጤና መድህን አገልግሎት ዳይሬክቶሬት እንደገለፁት የማህበረሰብ አቀፍ ጤና መድህን ሲገልፁት ማህበረሰብ አቀፍ ጤና መድህን እንደ ሀገርም እንደ ክልልም ተግባራዊ ለማድረግ ያስፈለገበት መሰረታዊ ምክንያት ዜጎች ጥሪት ወይም ሀብት ይኖራቸዋል ነገር ግን ጥሬ ገንዘብ በእጃቸው ባለመኖሩ ምክንያት ወደ ጤና ተቋም መሄድ ሲገባቸው የጥሬ ገንዘብ እጦት ስለሚከሰት በቤታቸው ሲታመሙ እናያለን ብለዋል፡፡

ሰዎች የጤና ተቋማት ጉብኝት ምጣኔአቸው እንዲጨምር ጤንነታቸው እንዲጠበቅ ፣ ጤንነታቸው ሲጠበቅ ደግሞ ምርታማ እንዲሆኑ ስለሚያግዝ እንዲሁም አቅምን ያላገናዘበ ድንገተኛ ህመም ቢከሰት የጤና መድህን ምዝገባ አድርጎ ደብተር ካለው ተገልጋይ መሆን ስለሚችል ነው ሲሉ አብራርተዋል፡፡

በዚህ የማህበረሰብ አቀፍ ጤና መድን ማዕቀፍ አባል ሊሆኑ የሚገባቸውን የማህበረሰብ ክፍሎች ስናይ በደሞዝ የማይተዳደሩ፣ ቋሚ ገቢ የሌላቸው በጥቃቅንና አነስተኛ የተደራጁ አርብቶ አደር እና አርሶ አደር የሆኑ ግለሰቦችን መሆኑን አስገንዝበዋል፡፡

አቶ ሄኖክ አክለውም እንደ ሀገር በ2003 ዓ.ም አስራ ሶስት የሙከራ ጤና መድህን እንቅስቃሴው የተጀመረ ሲሆን ዛሬ እንደ ሀገር ከ106 በላይ ወረዳዎች ተድራሽ ማድረጉን እንዲሁም በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል መንግስት 6 ዞኖችን ይዞ የማህበረሰብ አቀፍ ጤና መድህን ድጋፍ እያደረገ መሆኑን ገልፀዋል፡፡

በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ወስጥ አንዱ በሆነው የቤንች ሸኮ ዞን የማህበረሰብ አቀፍ ጤና መድህን አፈጻጸምን ሲታይ በዞኑ በ6 የገጠር ወረዳዎች እና 2 ከተማ አስተዳደሮች በድምሩ በ8 መዋቅሮች የማህበረሰብ አቀፍ ጤና መድህን ስራዎች ተግባራዊ እየተደረገ መሆኑን አስረድተዋል፡፡

በዞኑ 2016 ምጣኔ በተመለከተ አፈፃጸም ነባር አባላት እድሳት 53 ሺህ 289 በመቶኛ 86% ፣ አዲስ አባላት ማፍራት 15 ሺህ 416 በመቶኛ 32% አጠቃላይ አባላት ምጣኔ 67 ሺህ 705 በመቶኛ 63% ነው።

የሚዛን አማን ከተማ አስተዳደር 9 ሺህ 986 እና የሲዝ ከተማ አስተዳደር 2 ሺህ 9 በመሆኑ የከተማ አባላት 12 ሺህ 395 ሲሆኑ የቀሩት የገጠር አባላት 55 ሺህ 310 አጠቃላይ አባላት ምጣኔ 67 ሺህ 705 በመቶኛ ሲቀመጥም 63 መሆኑን አቶ ሄኖክ ገልፀዋል ።

መክፈል የማይችሉ ዜጎችን በመመልመል ከክልል መንግስት 40% ከዞን መንግስት 30% ከወረዳ መንግስት 30% የተናጠል ድጎማ ሲያደርጉ አፈፃጸማቸው 100% ነው ሲሉ አብራርተዋል፡፡

በ2016 ማህበረሰባችን የመመዝገብያ ክፍያ በገጠር 550 ብር በከተማ 650 ብር መሆኑን ገልፀው ለነባር ዕድሳት በገጠር 500ብር በከተማ 600 ብር መሆኑን አቶ ሄኖክ ተናግረዋል ።

በ2016 ከነባር አባላት እድሳትና ከአዲስ ገቢዎች 27 ሚሊዮን 413 ሺህ 841 ብር መሰብሰቡን ገልፀዋል ።

መክፈል ለማይችሉ ዜጎች በወረዳ 2 ሚሊዮን 380 ሺህ 95 ብር፣ በዞን 2 ሚሊዮን ብር በክልል 1ሚሊዮን 611ሺህ 819 ነጥብ 27 ሳንቲም መሆኑን አቶ ሄኖክ ጠቁመዋል።

አቶ ሄኖክ ቀጥለውም በዋናነት ተግባር በሀላፊነት ቴክኒካልና ፋይናንሻል ድገፍ በማድረግ የግንዛቤ ማስጨበጫ ትምህርት በመስጠት በሀላፊነት ለሚመሩ አመራሮችና ጤና ኤክስቴንሽኖች ከዞን እስከ ቀበሌ ድረስ በማውረድ የተጠናከረ የክትትልና ድጋፍ ሥራ በመሰራቱ የተገኘ መሆኑን አስረድተዋል።

በ2015 ዓ.ም ተገልጋዮች ወደ መንግስት ጤና ተቋም ሲሔዱ የአንዳንድ የባለሙያዎች የአገልግሎት አሰጣጥ እንዝላል መሆን እና የመደሃኒት አቅርቦት ችግር እንደነበረና ከዚህም መነሻ ነባር አባላት ቅሬታ እንደሚያነሡ ይህም ብቻ ሳይሆን የነባሩ አባላት አለመርካት አዲስ አባል ከማፍራት አንፃር ትልቅ ተግዳሮት እንደነበር ጠቁመው በአገልግሎት አሰጣጥና በመድሀኒት አቅርቦት ላይ እንደ ሀገር እየተሰራ መሆኑን ተናግረዋል።

አሁን ላይ ግን ይህንን ችግር ከዞንና ከወረዳ መንግስት ጋር እየተነጋገርን እራሱን የቻለ ስታንዳርድ ስላለው ችግሩ እየተፈታ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

በወረዳ መንግስት በኩል ለጤና ጣቢያ 250 ሺህ ብር ስታንዳርዱን የጠበቀ በጀት እንዲበጀት በማድረግና የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል ባለበት ለመደሃኒት ግዥ የሚሆን እስከ አንድ ሚሊየን ብር በዞኑ መንግስት በኩል እንዲበጀት በማድረግ የዚህ አባል ቅሬታ እንዲፈታ ከማድረግ አንፃር ሰፊ ውይይቶችን እያደረግንነው ሲሉ ገልፀዋል፡፡

ማንኛውም አባል ደብተር ከወሰደ መገልገል ያለበት እራሱና ያስመዘገባቸው ቤተሰቦቹ ብቻ እንጂ ሌላ ሰው አያካትትም በህግ አሰራር እንደሚያስቀጣና ከአባልነትም እስከ መሰናበት እንደሚያደርስ ገልጸዋል፡፡

ቀጣይ ሁሉም አባወራ እና እማውራ የማህበረሰብ አቀፍ የጤና መድህን አባል መሆን እንዳላባቸው በአዋጅ ቁጥር 1273/2014 ንዑስ አንቀጽ 13 መደንገጉን አቶ ሄኖክ አባጅፋር ገልፀው በ2017 ዓ.ም ሰፊ የንቅናቄው ስራዎችን በመስራት ምጣኔው ከፍ ለማድረግ ይሰራል ብለዋል።

አቶ ኤሊያስ ምናሴ የዞኑ ጤና መምሪያ ኃላፊ በማጠቃለያቸውም የማህበረሰብ ጤና መድህን ከጀመረ ወዲህ ወደ ህክምና ተቋማት የመምጣት ሁኔታ እየጨመረ መምጣቱን ጠቁመው በቀጣይ ዓመት የግንዛቤ ማስጨበጫን በማስፋት ነባር አባላት እያገኙ ያለውን ጥቅም እንዲገነዘቡ በማድረግ የተጠቃሚን ቁጥር እስከ 85 ከመቶ ለማድረስ እንደሚሰራ ተናግረዋል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Back To Top