የገበታ ለትውልድ ፕሮጀክት አካል የሆነው የደንቢ የመስህ ፕሮጀክት 372.5 ሄክታር ይዞታን የመከለልና ጋይድ ማፕ የማዘጋጀት ስራ እየተሰራ ነው፦ አቶ ጌታቸው ኮይካ

የገበታ ለትውልድ ፕሮጀክት አካል የሆነው የደንቢ የመስህ ፕሮጀክት 372.5 ሄክታር ይዞታን የመከለልና ጋይድ ማፕ የማዘጋጀት ስራ እየተሰራ ነው፦ አቶ ጌታቸው ኮይካ

ሚዛን አማን ፣ ነሀሴ 19/2015 ዞኑ የቱሪዝም ፣ የኮንፍረንስ ቱሪዝም ፣ የንግድና የኢንቨስትመንት ማዕከል ከመሆኑ ጋር ተያይዞ መስህቡ መገንባት ቅልቅ ፋይዳ ያለው ነው ብለዋል።

የቤንች ሸኮ ዞን ባህል ቱሪዝምና ስፖርት መምሪያ ኃላፊ አቶ ጌታቸው ኮይካ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ የደንቢ የመስህብ ፕሮጀክት እንደ ሀገር በገበታ ለትውልድ ከተያዙ 10 ግዙፍ ፕሮጀክቶች አንዱ መሆኑን ገልፀዋል።

ደንቢ የመስህብ ስፍራ ከ1972 ጀምሮ እስከ 1980ዎቹ አጋማሽ ድረስ ለበበቃ ፣ አማንና ሚዛን ዙሪያ ከተሞች የኤሌክትሪክ አገልግሎት ሲሰጥ የነበረ ታሪካዊ ሰው ሰራሽ ሀይቅና ፏፏቴዎችን የያዘ ስፍራ መሆኑን ገልፀዋል ።

ከ1990ዎቹ መጀመሪያ ጀምሮ የጊቤ የ24 ሰዓት ኤሌክትሪክ አገልግሎት መስጠትን ተከትሎ ደንቢ ስራውን አቋርጦ ወደ መስህብነት ስፍራ መቀየሩን ገልፀዋል። እንደ ዞን የሀገር ፣ የክልል መሪዎችን ጨምሮ በርካታ የሀገር ውስጥና የውጭ ሀገር ቱሪስቶች የጉብኝት ስፍራ በመሆን የዞኑን ገጽታ መገንባት መቻሉን ገልፀዋል።

አሁን በኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚንስትር ዶክተር አብይ አህመድ በገበታ ለትውልድ ከተያዙ 10 ፕሮጀክቶች አንዱ በመሆን የተመረጠ ሲሆን በቅርቡም ከጠቅላይ ሚንስትር ጽህፈት ቤት ከፍተኛ አመራሮች ፣ መሀንዲሶችና አርክቴክቶች እንዲሁም የክልሉና የዞኑ ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች ስፍራው መጎብኘታቸውን ጠቁመዋል።

ከለውጡ ማግስት መንግስት የቱሪዝሙን ዘርፍ አቅም ከግምት ውስጥ በማስገባት እንደ ሀገር ብሎም በአፍሪካ ደረጃ ከቀዳሚ 5 የቱሪስት መዳረሻ ስፍራዎች አንዱ ለመሆን እየተሰራ ያለው ስራ ውጤታማ እየሆነ መምጣቱን ኃላፊው ጠቁመዋል።

ከዞን ከተማ ልማት ፣ ባህል ቱሪዝምና ስፖርት መመሪያና ሌሎች ባለድርሻ አካላትንና የመሀንዲሶች ቡድንን በማሳተፍ የምስህቡን ይዞታ የማካለል ፣ ከ3ተኛ ወገን ነጻ የማድረግና የጋይድ ማፕ ዝግጅት ስራው እየተጠናቀቀ መሆኑን ገልጸዋል።

በዚህም የደንቢ ሰው ሰራሽ ሀይቅና ፏፏቴ የመስህብ ስፍራን በ372.5 ሄክታር የማካለል ስራ እየተሰራ መሆኑን ጠቁመዋል። የሚዛን አማን ዘመናዊ የአውሮፕላን ማረፊያ ከመስህቡ በቅርብ ርቀት ላይ መሆኑ ፣ ዞኑ የቱሪዝም ፣ የኮንፍረስ ቱሪዝም ፣ የንግድና የኢንቨስትመንት ማዕከል ከመሆኑ ጋር ተያይዞ የጎብኚዎችን ቁጥር ከፍ እንደሚያደርገው ገልጸዋል።

የፕሮጀክቱ ወደ አካባቢው መምጣት ጋር ተያይዞ እንደ ዞን ያሉንን የቱሪዝም ፀጋዎች እንድናለማና ለቱሪስቶች ክፍት በማድረግ ከዘርፉ የሚገኘውን ገቢ ለማሳደግ አይን የከፈተ ፕሮጀክት ነው ብለዋል።

በተዘራ ጥላሁን

ድረ ገጽ፦ www.benchshekozonecom.gov.et
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/benchshekozonepublicrelationoffice
ዩትዩብ፦ https://youtube.com/@BenchShekoZoneGovernmentCommun?feature=share8
ቴሌግራም፦ https://t.me/bszgca
ትዊተር፦ https://twitter.com/BenchGov?t=V1DGL3YnPHirGEiTq-jh2A&s=09
ኢንስታግራም፦ https://instagram.com/benchshekozonepr?utm_source=qr&igshid=MzNlNGNkZWQ4Mg%3D%3D
ቲክቶክ፦ tiktok.com/@benchshekozonegov
በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Back To Top