የቤንች ሸኮ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ቀበሌ መንገሻ የፋይዳ ብሄራዊ የዲጂታል መታወቂያ በመመዝገብ በሚዛን አማን ከተማ አስጀመሩ።

የቤንች ሸኮ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ቀበሌ መንገሻ የፋይዳ ብሄራዊ የዲጂታል መታወቂያ በመመዝገብ በሚዛን አማን ከተማ አስጀመሩ።

በዛሬው እለት በሚዛን አማን ከተማ ብሄራዊ የዲጂታል መታወቂያ ምዝገብ ተጀምሯል።

የቤንች ሸኮ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ቀበሌ መንገሻ የሚዛን አማን ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አቶ ግሩም ተማምን ጨምሮ የዞንና የከተማ አስተዳደር ባለድርሻ አካላት በሚዛን የዞኑ ገቢዎች መምሪያ ውስጥ በአማን የከተማው ገቢዎች ጽ/ቤት ውስጥ በመገኘት በሁለት ማዕከላት የፋይዳ ብሄራዊ የዲጂታል መታወቂያ አስጀምረዋል።

የቤንች ሸኮ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ቀበሌ መንገሻ በተመዘገቡበትና ባስጀመሩበት ወቅት የብሄራዊ መታወቂያ በመላ ሀገሪቱ ዜጎች ማንኛውንም አገልግሎት እንዲያገኙ የሚያስችል እንደሆነም የተናገሩት።

የብሄራዊ መታወቂያ ለዜጎች ዲጂታል በሆነ መንገድ ማንነታቸውን እንዲያረጋገጡ የሚያስችል ነው ብለዋል።

የዲጂታል መታወቂያ ትግበራ ለአገሪቱ ዲጂታል ትራንስፎርሜሽን፣ እንዲሁም ለአሥር ዓመቱ የመንግሥት የልማት ዕቅድ ያለው አስተዋጽኦ ከፍተኛ መሆኑንም ጠቁመዋል።

የዲጂታል መታወቂያ የማንነት ስርቆትን እና ማጭበርበርን ለመዋጋት የሚረዳ በመሆኑ ሁሉም ነዋሪዎች ይህንን እድል በመጠቀም ለፋይዳ ብሔራዊ መታወቂያ ከሁለቱ የሚቀርባቸው ማዕከል ላይ በመገኘት እንዲመዘገቡ ጥሪ አስተላልፈዋል።

የሚዛን አማን ከተማ እተዳደር ዋና ከንቲባ አቶ ግሩም ተማም በበኩላቸው የፋይዳ ዲጂታል መታወቂያ እንደ ሀገርም ሆነ እንደከተማው ፋይዳው የጎላ በመሆኑ ሁሉም በመመዝገብ የዲጂታል መታወቂያ ባለቤት መሆን አለበት ብለዋል።

እንደ ከተማ የዲጂታል መታወቂያ ምቹ በሆነ መንገድ አገልግሎት እንዲሰጥ አስፈላጊውን ሁሉ እየተደረገ መሆኑን አብራርተዋል።

በዚህ ሂደት ማንኛውም የከተማዋ ነዋሪ ማንነቱን የሚገልፅ መታወቂያ በመያዝ በየማዕከላቱ በመገኘት አገልግሎቱን እንዲያገኙ ጥሪ አስተላልፈዋል።

One thought on “የቤንች ሸኮ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ቀበሌ መንገሻ የፋይዳ ብሄራዊ የዲጂታል መታወቂያ በመመዝገብ በሚዛን አማን ከተማ አስጀመሩ።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Back To Top