የቤንች ሸኮ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ቀበሌ መንገሻን ጨምሮ የምክር ቤት አባላት በሚዛን አማን ከተማ እየተከናወኑ የሚገኙትን የመሠረተ ልማት ስራዎች ጎበኙ።

የቤንች ሸኮ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ቀበሌ መንገሻን ጨምሮ የምክር ቤት አባላት በሚዛን አማን ከተማ እየተከናወኑ የሚገኙትን የመሠረተ ልማት ስራዎች ጎበኙ።

የሚዛን አማን ከተማ አስተዳደር ምክር ቤቱ 4ኛ ዙር 10 ዓመት የስራ ዘመን 27ኛ መደበኛ ጉባኤውን ዛሬ ማካሄድ ጀምሯል።

የቤንች ሸኮ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ቀበሌ መንገሻ ፤ የሚዛን አማን ከተማ አስተዳደር ዋና ከንቲባ አቶ ግሩም ተማምን ጨምሮ ከምክር ቤቱ አባላት ጋር ከጉባኤው ጎን ለጎን በከተማ አስተዳደሩ እየተከናወኑ ያሉ የመሠረተ ልማት ስራዎችን ጎብኝተዋል።

በጉብኝቱም በከተማው የኮብልስቶን ንጣፍ፤ የትምህርት ቤቶች መሰረተ ልማት ማሻሻል ያለበት ሂደትና የሚዛን አማን ከተማ አስተዳደር ምክር ቤት ህንፃ ግንባታ ሂደት ተጎብኝተዋል።

ከ111 ሚሊዮን ብር በላይ ወጪ የሚገነባው የሚዛን አማን ከተማ አስተዳደር ምክር ቤት ህንፃ ግንባታ በሁለት ፈርጅ የሚከናወን ሲሆን የመጀመሪያው ፈርጅ ከ2 ሺህ ህዝብ በላይ መያዝ የሚችል የአዳራሽ በ19 ሚሊዮን ብር ተገንብቶ በዘንድሮው አመት የሚጠናቀቅ መሆኑ በጉብኝቱ ወቅት ተገልጿል።

በጉብኝቱ ወቅት በከተማው እየተከናወኑ ያሉ አበረታች ስራዎችን አጠናክሮ በማስቀጠል በቀጣይ ለህዝቡ የመሰረተ ልማት ተደራሽነት ላይ ትኩረት መስጠት ይገባል ተብሏል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Back To Top