የቤንች ማጂ ልማት ማህበር የባለ ልዩ ተሰጥኦ ተማሪዎች አዳሪ ትምህርት ቤት ጅማሮ አበረታችና ተስፋ ሰጪ ነው ፦ አቶ ቀበሌ መንገሻ

የቤንች ማጂ ልማት ማህበር የባለ ልዩ ተሰጥኦ ተማሪዎች አዳሪ ትምህርት ቤት ጅማሮ አበረታችና ተስፋ ሰጪ ነው ፦ አቶ ቀበሌ መንገሻ

ሚዛን አማን ፣ ነሀሴ 27/2015 ልማት ማህበሩ የአዳሪ ትምህርት ቤቱን የ2015 አፈጻጸም ፣ የ2016 የተማሪ ቅበላ ዕቅድና የባለድርሻ አካላት ሚና ላይ በዞኑ ካቢኔ መሰብሰቢያ አዳራሽ ውይይት አድርጓል።

የቤንች ማጂ ልማት ማህበር የባለ ልዩ ተሰጥኦ ተማሪዎች አዳሪ ትምህርት ቤት በዞኑ መንግስት ፣ በልማት ማህበሩ ቦርድ ፣ በሚዛን ቴፒ ዩኒቨርስቲና በባለድርሻ አካላት ርብርብ በ2015 የትምህርት ዘመን ከዞኑ 53 ባለ ልዩ ተሰጥኦ ተማሪዎችን በመመልመልና በመቀበል ስራውን ጀምሯል።

የቤንች ማጂ ልማት ማህበር ዋና ስራ አስኪያጅ አቶ አጽናኝ ፈለቀ የአዳሪ ትምህርት ቤቱን የ2015 አፈጻጸምና የ2016 ጠቋሚ ዕቅድ ሲያቀርቡ እንደተናገሩት በተጠናቀቀው የትምህርት ዘመን በዞኑ ከሁሉም ትምህርት ቤቶች ከፍተኛ ውጤት ላስመዘገቡ ተማሪዎች የመግቢያ ፈተና በማዘጋጀት 39 ወንድ ፣ 14 ሴት በድምሩ 53 ተማሪዎችን ተቀብሎ ሲያስተምር መቆየቱን ገልጸዋል።

በትምህርት ዘመኑ 3 ተማሪዎች በጤና እክልና በማህበራዊ ችግር ትምህርታቸውን ያቆሙ ሲሆን 50 ተማሪዎች እስከ ትምህርት ዘመኑ መጨረሻ መዝለቃቸውን ጠቁመዋል። በተደረገ የውጤት ምዘናም 32 ተማሪዎች ከ85 በላይ ፣ 14 ተማሪዎች ከ75 በላይ እንዲሁም 4 ተማሪዎች ከ60 በላይ አማካይ ያገኙ ሲሆን ጥቅል የትምህርት ቤቱ አማካይ ውጤት 97 እንዲሁም ዝቅተኛው 63 መሆኑን ገልጸዋል።

በ2016 የትምህርት ዘመን 50 አዳዲስ ተማሪዎችን ለመቀበል በዕቅድ የተያዘ ሲሆን አምና በትምህርት ዘመኑ በምልመላ ፣ የቤተ መጻህፍት ፣ የትራንስፖርት ፣ የመምህራን የማበረታቻ ክፍያ ላይ የታዩ ችግሮችን ከወዲሁ ለማረምና በፍጥነት ወደ ስራ መግባት ያስፈልጋል ብለው ወረዳና ከተማ አስተዳደሮች ቋሚ ድጋፍ ሊያደርጉ ይገባል ብለዋል።

የሚዛን ቴፒ ዩኒቨርስቲ ፕሬዝዳንት ዶክተር አህመድ ሙስጠፋ በመድረኩ እንደተናገሩት በ2015 የትምህርት ዘመን በርካታ ችግሮች ቢኖሩም ዞኑ ፣ ልማት ማህበሩና ባለድርሻ አካላት ተቀናጅተው በመስራታቸው ችግሮችን በመቅረፍ መስራት ተችሏል ብለዋል። በቀጣይም ዩኒቨርሰቲው በማኔጅመንት በመነጋገር ውሳኔውነ ያሳውቃል ብለዋል።

የልማት ማህበሩ የቦርድ አባልና በዩኒቨርሲቲው የተማሪዎች አገልግሎት ምክትል ፕሬዝዳንት ዶክተር ካሳሁን ሙላት በበኩላቸው ልማት ማህበሩ የዞኑን ፣ የልማት ማህበሩንና የባለድርሻ አካላትን አቅም ባገናዘበ መልኩ ተማሪዎችን ሊቀበል ይገባል ብለው የወረዳና የከተማ አስተዳደሮች ተሳትፎና ዕገዛ ያስፈልጋል ብለዋል።

የዞኑ ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ዮናስ ኬና እንደተናገሩት ልማት ማህበሩ ተማሪዎቹን የመለመለበት ፣ ያስተማረበትና አባላትን ለማፍራት የሄደበት ርቀት የሚደነቅና የሚበረታታ ነው ብለዋል። በቀጣይም የምልመላ ስራው ከችግር የጸዳና ውጤትን ብቻ መሰረት ሊያደርግ ይገባል ብለዋል።

የዞኑ ምክትል አስተዳዳሪና የፋይናንስና ኢኮኖሚ ልማት መምሪያ ኃላፊ አቶ ሳሙኤል አሰፋ በበኩላቸው የሚዛን ቴፒ ዩኒቨርስቲ አምና ለተማሪች ማደሪያ ፣ መመገቢያና ግቢውን በመፍቀድ ላደረገው እገዛ ምስጋና አቅርበዋል። ከተጋገዝንና ከተነጋገርን ሁሉም ነገር የሚቻልና የማይፈታ ችግር አለመንሩን ያሳየ መሆኑንም ጠቁመዋል።

የቤንች ሸኮ ዞን ዋና አስተዳዳሪና የልማት ማህበሩ የበላይ ጠበቂ አቶ ቀበሌ መንገሻ በመድረኩ ማጠቃለያ እንደተናገሩት አምና የሚዛን ቴፒ ዩኒቨርስቲ ጋር በመነጋገር ትልቅ ስራ መሰራቱን ገልፀው በተያያዘው የትምህርት ዘመንም 50 አዲስ ተማሪዎች ምልመላ ይደረጋል ብለዋል።

የተማሪዎቹ የውጤት ትንተና አስደሳችና ተስፋ ሰጪ ነው ያሉት አቶ ቀበሌ ዘንድሮ ወረዳና ከተማ አስተዳደሮች ልማት ማህበሩን ሊደግፉ እንደሚገባ ጠቁመው የሚዛን ቴፒ ዩኒቨርስቲም በምን መልኩ እንደሚያግዝ ሊያሳውቀን ይገባል ብለዋል ዋና አስተዳዳሪው።

በተዘራ ጥላሁን

ለበለጠ መረጃ ፦
ድረ ገጽ፦ www.benchshekozonecom.gov.et
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/benchshekozonepublicrelationoffice
ዩትዩብ፦ https://youtube.com/@BenchShekoZoneGovernmentCommun?feature=share8
ቴሌግራም፦ https://t.me/bszgca
ትዊተር፦ https://twitter.com/BenchGov?t=V1DGL3YnPHirGEiTq-jh2A&s=09
ኢንስታግራም፦ https://instagram.com/benchshekozonepr?utm_source=qr&igshid=MzNlNGNkZWQ4Mg%3D%3D
ቲክቶክ፦ tiktok.com/@benchshekozonegov
በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Back To Top