የመሠረተ ልማት ጥያቄ ችግሮች ን ለመፍታት ትኩረት ተሰጥቶት እንዲሰራ የቤንች ሸኮ ዞን ዋና አስተዳዳሪ ክቡር አቶ ቀበሌ መንገሻ ጠየቁ።

የመሠረተ ልማት ጥያቄ ችግሮች ን ለመፍታት ትኩረት ተሰጥቶት እንዲሰራ የቤንች ሸኮ ዞን ዋና አስተዳዳሪ ክቡር አቶ ቀበሌ መንገሻ ጠየቁ።

የኢፌዴሪ ህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት በቤንች ሸኮ ዞን የክልልና የህዝብ ተወካዮች በተገኙበት ውይይት አካሂደዋል።

የደቡብ ምዕራብ ህዝቦች ክልላዊ መንግስት ከተደራጁ ጀምሮ በክልሉ ሠላም ፣ ልማትና ወንድማማችነት ላይ በሁሎም ዞኖችና ወረዳዎች ሲሰራ መቆየቱን የኢፌዴሪ ህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባል የተከበሩ አቶ ዳውድ መሀመድ ገልጸዋል ።

የመሠረተ ልማት ጥያቄ ችግሮችን መፍታት እንድቻል ጥያቄዎችን ማዕከል ባደረገ መልኩ እየተሰራ ነው ብለው ክልላችን ለሀገር እያበረከተ ካለው ድርሻ ረገድ የእይታ ክፍተቱን ለመሙላት ትግል እየተደረገ መሆኑን አስረድተዋል።

የቤንች ሸኮ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ቀበሌ መንገሻ በበኩላቸው የኢፌዴሪ ህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት የዞኑን ነባራዊ ሁኔታን ለማየት መምጣታቸውን አመስግነው በተለይም በፌደራል እና ክልል ተጀምረው ባልተጠናቀቁ መሠረተ ልማቶች ላይ ማብራሪያ ሰጥተዋል።

በዚህም የሚዛን ቴፒ አስፓልት መንገድ ከተጀመረ ረጅም ጊዜ የወሰደ ቢሆንም በተያዘለት ጊዜ ውስጥ አልተጠናቀቀም ያሉት አቶ ቀበሌ የሚዛን ጂማ አስፓልት መንገድ ላይ ያለው የጥራት ችግር ዘላቂ በሚሆንበት ደረጃ ላይ በትኩረት አለመሠራቱ የመልካም አስተዳደር ችግር እየሆነ መጥተዋል ብለዋል።

አቶ ቀበሌ አክለውም የዋቻ ማጂ መንገድ መዘገየት በመንገዱ ናዳ መኖሩ እያስቸገረ በመሆኑ ስራው ፈጥኖ እንዲጀምር የጠየቁት ዋና አስተዳዳሪው የቂጤ ደብረወርቅ ጊጪ አድርጎ ምዕራብ ኦሞ ዞን በጎሪ ጌሻ የሚያወጣ አስፓልት መንገድ እንዲሰራ ጠይቀዋል።

በገጠር መንገድ ደረጃ ተጀምረው ያልተጠናቀቁ ድልድዮችና መንገዶች በህዝባችን የመልካም አስተዳደር ችግር እየሆነ ነውም ብለዋል።

የሚዛን አማን ዓለም አቀፍ አየር መንገድ በክቡር ጠቅላይ ሚኒስተር ዶ/ር ዐቢይ አህመድ በ16/10/2013 ዓ/ም የመሰረተ ድንጋይ ተጥሎ 282 ሄክታር መሬት ተከልሎ ቦታውን ነፃ ለማድረግ የካሳ ክፊያው እየተከፈለ እንዳለ አቶ ቀበሌ ተናግረዋል።

ይሁን እንጂ የካሳ ክፍያው በጣም ከፍተኛ በመሆኑ የዞኑን አቅም መፈተኑን የገለጹት አቶ ቀበሌ በዘንድሮው ዓመት ለሚነሱ ባለይዞታዎች ክፍያ ለመፈፀም 70 ሚሊዮን ብር ስለሚያስፈልግ የሚመለከተው አካል ቢያግዘን ብለዋል።

ከውሃ ሽፋን ረገድ ዞናችን 33.3 በመቶ ላይ ይገኛል ያሉት ዋና አስተዳዳሪው ከተጠናቀቀው በጀት ዓመት ጀምሮ በተሰራው ስራ መሻሻሎች መኖራቸውን ተናግረው ቀጣይ ትኩረት ተሰጥቶ ይሰራል ብለዋል።

አቶ ቀበሌ መንገሻ በተጨማሪ ዞኑ ሰፊ የሆነ የፍራፍሬ ምርቶች በመኖራቸው እዚሁ በማምረት ለገበያ ለማቅረብ ፋብሪካ ባለመኖሩ እየባከነ ስለመጣ የትኛውንም የኢንቨስትመንት አማራጮች ለመጠቀም እየተሰራም ነው ብለዋል።

በዞኑ በሁሉም መዋቅሮች የወባ ወረርሽኝ ከጊዜ ወደጊዜ እየተባባሰ በመምጣተ የመድሀኒት አቅርቦት ችግር በመኖሩ አገልግሎት ላይ በስፋት ችግር ፈጥሯል ብለዋል። አያይዘውም ዋና አስተዳዳሪው በዞኑ የመጀመሪያ ሆስፒታል አንድ ብቻ መኖሩን ገልፀው ለህዝቡ የጤና አገልግሎት የሚስተዋለውን አቅርቦት ችግር ለመቅረፍ የሚመለከተው አካል አስፈላጊውን ድጋፍ እንዲያደርግ ጠይቀዋል።

በመድረኩ የ6ቱም ዞኖች የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት የክልልና የዞን ምክር ቤት አባላት የዞን እና የወረዳ ከፍተኛ አመራሮች፤ የሀገር ሽማግሌዎች፤ የጎሳ መሪዎች ተሳትፈዋል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Back To Top