የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት በሚዛን ቴፒ ዩኒቨርስቲ ቲቺንግ ሆስፒታል በመገኘት የሆስፒታሉን አጠቃላይ የስራ እንቅስቃሴና ግንባታዎችን ተዘዋውረው ጎበኙ።

የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት በሚዛን ቴፒ ዩኒቨርስቲ ቲቺንግ ሆስፒታል በመገኘት የሆስፒታሉን አጠቃላይ የስራ እንቅስቃሴና ግንባታዎችን ተዘዋውረው ጎበኙ።

ሚዛን አማን ፣ ነሀሴ 21/2015 አባላቱ በመጀመሪያ ቀን በከሰዓት ውሎአቸው በሆስፒታሉ በመገኘት አጠቃላይ ስራዎችንና የጤና ኮሌጅ ግንባታዎችን ጎብኝተዋል።

የሚዛን ቴፒ ዩኒቨርስቲ ቲቺንግ ሆስፒታል በቀድሞ የሚዛን አማን አጠቃላይ ሆስፒታል በሚል በ1972 ዓመተ ምህረት አካባቢ ለ60ሺ ህዝብ አገልግሎት ይሰጣል ተብሎ የተገነባ ነው።

ከ2008 ዓመተ ምህረት ጀምሮ በሚዛን ቴፒ ዩኒቨርስቲ ቲቺንግ ሆስፒታል ሆኖ የተጠቃለለ ሲሆን ዛሬ ላይ ለቤንች ሸኮ ፣ ምዕራብ ኦሞ ፣ ማጃንግ ዞን ፣ አኙዋ ዞን እንዲሁም በከፊል ለካፊና ሸካ ዞን ህዝቦች በአመት ከ1.5 ሚሊየን በላይ ሰዎችን ያስተናግዳል።

በተለይ ሆስፒታሉ ከፍተኛ ቁጥር ያለው ተገልጋይ ያለው ከመሆኑ ጋር ተያይዞ የተኝቶ ህክምና ክፍሎች ፣ የተመላላሽ ህክምና ፣ ለድንገተኛ አደጋ ፣ የአጥንት ፣ የቀዶ ጥገና ክፍሎች እንዲሁም እንደ ሲቲ ስካን አይነት የህክምና ቁሳቁስ አለመኖር የሪፈራል ቁጥሩንና በአሰራር ላይ ከፍተኛ ቅሬታን እየፈጠረ እንደሚገኝ የሆስፒታሉ ቺፍ ዳይሬክተር ዶክተር እርቂሁን ጳውሎስ ለምክር ቤቱ አባላት ገልጸዋል።

ከዚህ ቀደም ከመድኃኒት አቅርቦት ጋር ተያድዞ በተገልጋዮች ይነሱ የነበሩ የነበሩ ቅሬታዎችን ለመፍታት ከፍተኛ ጥረት ተደርጓል ብለዋል። ከካርድ ክፍልና ተያያዥ ጉዳዮች ላይ የሚነሱ ችግሮችን ለመፍታት ጥረት እየተደረገ ነው ብለዋል።

ቺፍ ዳይሬክተሩ ሆስፒታሉ ላለፉት 40 ዓመታትና ከዚያ በላይ ምንም አይነት ማስፋፊያ ያልተደረገለትና አሁን ላይ ተጨማሪ የማስፋፊያ ግንባታዎች ካልተከናወኑ ችግሩ እየተባባሰ እንደሚመጣ ገልጸዋል። የምክር ቤቱ አባላትም የችግሩን ስፋትና ጥልቀት በመረዳት ለሚመለከታቸው አካላት እንዲያደርሱ ጠይቀዋል።

የተወካዮች ምክር ቤት አባላቱ በጠዋቱ ጉብኝታቸው የገበታ ለትውልድ የግንባታ አካል የሆነውን የደንቢ ሰው ሰራሽ ኃይቅና ፏፏቴ ፣ የሚዛን አማን ዘመናዊ አውሮፕላን ማረፊያ ግንባታና የሴካ አግሮ ፕሮሰሲንግ የማንጎ ልማት ስራዎችን ጎብኝተዋል።

በነገው ዕለትም ከዞኑ ከፍተኛ አመራሮች ጋር የውይድት መድረክ የሚዘጋጅ መሆኑን ከወጣው መርሀ ግብር ለማወቅ ተችሏል።

በተዘራ ጥላሁን

ድረ ገጽ፦ www.benchshekozonecom.gov.et
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/benchshekozonepublicrelationoffice
ዩትዩብ፦ https://youtube.com/@BenchShekoZoneGovernmentCommun?feature=share8
ቴሌግራም፦ https://t.me/bszgca
ትዊተር፦ https://twitter.com/BenchGov?t=V1DGL3YnPHirGEiTq-jh2A&s=09
ኢንስታግራም፦ https://instagram.com/benchshekozonepr?utm_source=qr&igshid=MzNlNGNkZWQ4Mg%3D%3D
ቲክቶክ፦ tiktok.com/@benchshekozonegov
በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Back To Top