ከቤንች ሸኮ ዞን በ3 የስፖርት ዘርፎች 26 ስፖርተኞች ወደ ኢትዮጵያ ስፖርት አካዳሚ መግባታቸው ተገለፀ

ከቤንች ሸኮ ዞን በ3 የስፖርት ዘርፎች 26 ስፖርተኞች ወደ ኢትዮጵያ ስፖርት አካዳሚ መግባታቸው ተገለፀ።

ሚዛን አማን ነሀሴ 16/2015 የዞኑ ባህል ፣ ቱሪዝምና ስፖርት መምሪያ ኃላፊ አቶ ጌታቸው ኮይካ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ያካዳሚውን መመልመያ መስፈርት ያሟሉ 26 ስፖርተኞች ወደ አካዳሚው እንደሚሄዱ ገልፀዋል።

የቤንች ሸኮ ዞን ባህል ፣ ቱሪዝምና ስፖርት መምሪያ ኃላፊ አቶ ጌታቸው ኮይካ በቢሮአቸው በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ የኢትዮጵያ ስፖርት አካዳሚ ከክልሉ ተተኪ ስፖርተኞችን በ4 የስፖርት አይነቶች መልምሎ ወደ አካዳሚው በማስገባትና ስልጠና ለመስጠት በቤንች ሸኮ ዞን 2 ከተማ አስተዳደሮችን ጨምሮ በሁሉም ወረዳዎች ስፖርተኞችን የመመልመል ስራ ሲሰራ መቆየቱን ገልጸዋል።

አካዳሚው በአትሌቲክስ ፣ በእግር ኳስ ፣ በቴኳንዶና በቦክስ ስፖርቶች የምልመላ ስራውን የሰራ ሲሆን እንደ ዞን ከቦክስ ስፖርት በስተቀር በ3 የስፖርት ዘርፎች 26 ስፖርተኞች የምዘና መስፈርቱን አሟልተው መመረጣቸውን ገልጸዋል።

በዚህም በእግር ኳስ 6 ፣ በበአትሌቲክስ 13 ፣ በሴቶች እግር ኳስ 4 እንዲሁም በቴኳንዶ 2 ስፖርተኞች ምልመላውን በብቃት በማለፍ ወደ አካዳሚው ለመግባተ መቻላቸውን ገልጸዋል። ዞኑ በሁሉም የስፖርት አይነቶች በርካታ ተተኪ ስፖርተኞች እንዳሉት ታይቷል ያሉት ኃላፊው ከቦክስ አንጻር በርካታ የቴክኒክ ስራዎችና ልምዶችን ለመስጠት አካዳሚው ቃል መግባቱን ጠቁመዋል።

እንደ ክልል ከተመለመሉ ስፖርተኞች ውስጥ ዞኑ ከፍተኛውን ቁጥር እንደያዘ የተናገሩት ኃለፊው በቀጣይ አካዳሚው የመግቢያ ምዘና ከሰጠ በኀላ ሀገርን ወክለው የሚሳተፉ ስፖርተኞች እንደሚሆኑም ገልጸዋል።

ኃላፊው አክለውም በባህል ዘርፉ በርካታ የዞኑን ባህል ፣ እሴት ፣ ወግና ስርዓት የሚያንፀባርቁ ስራዎች እየተሰሩ መሆናቸውን ገልጸዋል። በዞኑ የቤንችና የሸኮ የዘመን መለወጫ ክብረ በዓላትን ለማክበር ቀደም ተብሎ ከባህል አዋቂዎችና ከሀገር ሽማግሌዎች ጋር የውይይት መድረክ ተዘጋጅቶ እንደነበርም ጠቁመዋል።

በቅርቡ ከምሁራንና ከዘርፉ ባለሙያዎች ጋር ተመክሮ ሙያዊ አስተያየት ተሰጠበት ወደ ስራ እንደሚገባ ኃላፊው አቶ ጌታቸው ጠቁመዋል።

በተዘራ ጥላሁን

ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/benchshekozonepublicrelationoffice
ዩትዩብ፦ https://youtube.com/@BenchShekoZoneGovernmentCommun?feature=share8
ቴሌግራም፦ https://t.me/bszgca
ትዊተር፦ https://twitter.com/BenchGov?t=V1DGL3YnPHirGEiTq-jh2A&s=09
ኢንስታግራም፦ https://instagram.com/benchshekozonepr?utm_source=qr&igshid=MzNlNGNkZWQ4Mg%3D%3D
ቲክቶክ፦ tiktok.com/@benchshekozonegov
ድረ ገጽ፦ www.benchshekocommunication.gov.et
በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Back To Top