ኢትዮጵያ የብሪክስ አባል መሆኗ ትልቅ ዲፕሎማሲያዊ ድል ነዉ::የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልላዊ መንግስት

ኢትዮጵያ የብሪክስ አባል መሆኗ ትልቅ ዲፕሎማሲያዊ ድል ነዉ::የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልላዊ መንግስት

የመግለጫዉ መሉ ቃል ቀጥሎ ቀርቧል።

” የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልላዊ መንግስት ሀገራችን ኢትዮጵያ የብሪክስ አባልነት ጥያቄዋ ተቀባይነት በማግኘቱ ለመላዉ ኢትዮጵያዊን እንኳን ደስ አለችሁ!እንኳን ደስ አለን ለማለት ይወዳል።

ሀገራችን የብሪክስ አባልነት ጥያቄ ካቀረቡ 40 በላይ ሀገራት ውስጥ መስፈርቶችን አሟልታ ጥያቄዋ ተቀባይነት ማግኘቱ ትልቅ ዲፕሎማሲያዊ ድል ነዉ።

ኢትዮጵያ ብሄራዊ ጥቅሟን ለማስከበር ከሁሉም ሀገራት ጋር መርህ በተመሰረተ አኳሃን አብራ ለመስራት ያላትን ቁርጠኝነት የሚያሳይ መሆኑን የሚያረጋግጥ ነው።

ይህ ትልቅ ድል በከፍተኛ የዲፕሎማሲ ጥረት የተገኘ በመሆኑ በሂደቱ የተሳተፉትን
ባለድርሻ አካላት የክልላችን መንግስት ያመሰግናል።

የኢፌዲሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አህመድ ለሰጡት ስኬታማ አመራር ምስጋናችን ከፍ ያለ ነዉ።

የብራዚል፣ የህንድ፣ የቻይና፣ የራሽያ እና የደቡብ
አፍሪካ መንግስታት ኢትዮጵያ የአባልነት ጥያቄዋ አዎንታዊ ምላሽ እንዲያገኝ ላበረከቱት አስተዋፅኦ ምሥጋናችን ላቅ ያለ ነው::

ኢትዮጵያ የብሪክስ አባል መሆኗ ያለው ኢኮኖሚያዊ ፋይዳ ትልቅ ነዉ፤ከአባል ሀገራት ጋር የውጭ ቀጥታ ኢንቨስትመንት በመሳብ የቴክኖሎጂ እና የዕውቀት ሽግግርን በመፍጠር የሀገራችንን የኢኮኖሚ ዕድገት በማፋጠን ወደ ብልፅግና የምናደርገውን ጉዞ የሚያፋጥን ነዉ ።

የብሪክስ አባል ሀገራት ኢኮኖሚያቸው በፍጥነት እያደገ ያለ መሆኑንና ትልቅ የህዝብ ቁጥር
እና ሰፊ የገበያ ዕድል ያላቸው በመሆኑ ለኢትዮጵያ የወጪ ንግድ ትልቅ አቅም የሚፈጥር ነው ።

ኢትዮጵያ ከአባል ሀገራቱ ጋር በመተባበር የመሰረተ ልማት አቅሟን ለማሳደግ ዕድል በመሆኑ በዓለም አቀፍ መድረኮች የኢትዮጵያን ተሰሚነት ከፍ የሚያደርግ በመሆኑ በአለም አቀፍ መድረክ ፍትህ እና ርትዕ እንዲሰፍን ሀገራችን የበኩሏን ሚና ለመወጣት ዕድል የፈጠረና በአጠቃላይ በዲፕሎማሲው መስክ ያገኘነውን ድል እንደ ስንቅ ተጠቅመን በሀገራችን ሰላም: ልማትና ዴሞክራሲ በማስፈን ሁለንተናዊ ብልፅግና ለማረጋገጥ የጀመርናቸውን ዘርፈብዙ ተግባራትን አጠናክረን እንዲንቀጥል ጥሪያችንን እናስተላልፋለን። “

የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል መንግስት

ነሐሴ 19 ቀን 2015 ዓ.ም

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Back To Top