አርሶ አደሩ በበልግ ወቅት የለሙና የደረሱ ምርቶችን በአግባቡ በመሰብሰብ ተጠቃሚ ሊሆን እንደሚገባ ተመላከተ

አርሶ አደሩ በበልግ ወቅት የለሙና የደረሱ ምርቶችን በአግባቡ በመሰብሰብ ተጠቃሚ ሊሆን እንደሚገባ ተመላከተ

አርሶ አደሩ በበልግ ወቅት የለሙና የደረሱ ምርቶችን በአግባቡ በመሰብሰብ ተጠቃሚ ሊሆን እንደሚገባ የቤንች ሸኮ ዞን ግብርና አካባቢ ጥበቃ ህብረት ሥራ መምሪያ አስታውቋል።

በዞኑ በአሁን ሰዓት በስፋት የበቆሎና የስንዴ ምርቶች የሚሰበሰብበት በመሆኑ ለውጤታማነቱ ሁሉም የድርሻውን ሊወጣ እንደሚገባም መምሪያው ገልጿል።

በበልግ ወቅት በዋና ዋና እና በሆርቲካልቸር ሰብሎች 91ሺህ 768 ሄክታር መሬት በዘር ለመሸፈን ታቅዶ 163ሺሀ 568 ሄክታር መሬት በላይ ማሳካት መቻሉን የዞኑ ግብርና አካባቢ ጥበቃ ህብረት ሥራ መምሪያ ኃላፊ አቶ መስፍን ጉብላ ተናግረዋል።

በዚህም በዞኑ በአገዳ 66ሺህ 290 ሄክታር እና በብዕር ሰብሎች 15 ሺህ 97 ሄክታር መሬት ማልማት መቻሉን ኃላፊው ገልፀው የደረሱ ምርቶችን አርሶ አደሩ በወቅቱን በመሰብሰብ ተጠቃሚ ሊሆኑ እንደሚገባቸውም አስገንዝበዋል።

አርሶ አደሩ ምርቱ እንዳይበላሽ ከተለያዩ ተባዮች በመከላከልና በመጠበቅ በአግባቡ ሰብሰቦ ለግብይት ማቅርብ እንደሚጠበቅበትም አቶ መስፍን አስታውቀዋል።

በመኸር ወቅት የደረሱ ምርቶችን የመሰብሰብ ተግባር በሁሉም አካባቢዎች ተጠናክሮ ሊቀጥል እንደሚገባ ኃላፊው አውስተው አምራች አርሶ አደሩ በግልም ሆነ ቤተሰብ ደረጃ በትኩረት ሊሰራ እንደሚገባም አስገንዘበዋል፡፡

በአሁን ሰዓት በዞኑ በመሰብሰብ ላይ ከሚገኙ ምርቶች አንዱ የስንዴ ምርት በመሆኑ ከለማው 603 ሄክታር ማሳ 521 ሄክታር ወደ 9ሺህ 602 ኩንታል ምርት መሰብሰቡ በሌሎችም አካባቢዎች ተጠናክሮ እንዲቀጥል አሳስበዋል። ደሬቴድ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Back To Top