ትምህርት ቤቶችን ምቹ የመማሪያ አካባቢና በግብዓት ማጠናከር የተማሪን ውጤትና ስነ-ምግባር በማሻሻል ረገድ የሚያበረክተው ሚና የጎላ መሆኑ ተገለጸ፡፡

ትምህርት ቤቶችን ምቹ የመማሪያ አካባቢና በግብዓት ማጠናከር የተማሪን ውጤትና ስነ-ምግባር በማሻሻል ረገድ የሚያበረክተው ሚና የጎላ መሆኑ ተገለጸ፡፡

ነሐሴ 20/2015 ሚዛን አማን፡ የቤንች ሸኮ ዞን ትምህርት መምሪያ በ2016 በጀት ዓመት በትምህርት ዝግጅት ምዕራፍ እየተከናወኑ ያሉ ተግባራት ዙሪያ የሚመለከታቸዉን ባለድርሻ አካላት በማሳተፍ በሚዛን አማን እየገመገመ ነው፡፡

የቤንች ሸኮ ዞን ትምህርት መምሪያ ኃላፊ አቶ ግዛው ኃይሌ እንደገለጹት የ2016 በጀት ዓመት የመማር ማስተማር ስራ ለመጀመር ክረምቱን በሙሉ የቅድመ ዝግጅት ስራ ሲሰራ መቆየቱን አስረድተዋል፡፡

በዚህም መሠረት የክረምት ማጠናከሪያ ትምህርት መስጠት ፣ ለተማሪዎች ምቹ የመማር ማስተማር አካባቢን መፍጠር ፣ የመጽሐፍ ህትመትን የሚያግዙ ግብዓቶች የማሰባሰብ ፣ የተጀመረዉን የትምህርት መርሃ ግብር በተጠናከረ መልኩ ማስቀጠልና የትምህርት ቤቶችን መሠረተ ልማት የማሟላት ተግባራት በቁልፍ ተግባር ተይዘዉ ሲተገበሩ መቆየታቸውን ኃላፊዉ አብራርተዋል፡፡

ተግባራቱን ለማከናወን የተደራጀ ዕቅድ በማዘጋጀት ከትምህርት ቤት እስከ ዞን ያሉ ባለድርሻ አካላት ፣ የትምርት ሴክተር አመራሩና ባለሙያዎች ተሳትፈዉ እና መክረዉበት ተግባናዊ እንቅስቃሴ እየተከናወነ መቆየቱን የገለጹት አቶ ግዛው የቅድመ ዝግጅት ምዕራፍ የመጀመሪያዉ ዙር የደረሰበትን እየገመገሙ መሆኑን ጠቅሰዋል፡፡

ኃላፊዉ አክለዉም በግምገማዉ በጥንካሬና በጉድለት የተለዩት ተግባራት ስራዉን በቀጥታ ለሚመለከታቸዉ አካላት ቆጥሮ በመስጠት በቀሩት ጊዜያት ዉስጥ በማጠናቀቅ ለመማር ማስተማር ስራ ምቹ አካባቢ እንደሚፈጠርም ተናግረዋል፡፡

የመማር ማስተማሩን ስራ በአዲስ መልክ በ2016 የትምህርት ዘመን ለመጀመር 12 አጀንዳዎች ተለይተዉ በአራት የተግባር ምዕራፎች እንደሚከናወኑ ያብራሩት ኃላፊዉ አጀንዳዎቹ በፕሮጀክት መልክ ተወስደዉ በአዲስ ፕላትፎርም በየደረጃዉ ተግባሩን የሚመራ ቡድን ይደራጃልም ብለዋል፡፡

ከዞን መምሪያ እስከ ትምህርት ቤት በመናበብ ተግባራት በተቆጠረ መልኩ በጊዜና በጥራት ማዕከል አድርጎ በማከናወን የተማሪን ዉጤትና ስነ-ምግባር ለማሻሻል ከምን ጊዜም በላይ ትኩረት ተሰጥቶ እንደሚሰራም አቶ ግዛው ኃይሌ አሳስበዋል፡፡

በካሳሁን ገ/ሚካኤል

በተጨማሪም ሌሎች መረጃዎችን በተለያዩ አማራጮችን በመጠቀም ይከታተላሉ
ድረ ገጽ፦ www.benchshekozonecom.gov.et
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/benchshekozonepublicrelationoffice
ዩትዩብ፦ https://youtube.com/@BenchShekoZoneGovernmentCommun?feature=share8
ቴሌግራም፦ https://t.me/bszgca
ትዊተር፦ https://twitter.com/BenchGov?t=V1DGL3YnPHirGEiTq-jh2A&s=09
ኢንስታግራም፦ https://instagram.com/benchshekozonepr?utm_source=qr&igshid=MzNlNGNkZWQ4Mg%3D%3D
ቲክቶክ፦ tiktok.com/@benchshekozonegov
በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Back To Top