ብሔራዊ ቡድኑ ነገ ከግብፅ ጋር ለሚያደርገው ጨዋታ የመጨረሻ ልምምዱን አከናወነ

ብሔራዊ ቡድኑ ነገ ከግብፅ ጋር ለሚያደርገው ጨዋታ የመጨረሻ ልምምዱን አከናወነ


የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ከነገው የግብፅ ጨዋታ አስቀድሞ የመጨረሻ ልምምዱን ጨዋታውን በሚያደርግበት ጁን 30 ስታዲየም አድርጓል።

ሁሉም የስብስቡ አባላት በተሟላ ጤንነት ልምምዳቸውን መስራታቸውን ከኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

የግብፅ እና የኢትዮጵያ የአፍሪካ ዋንጫ የመጨረሻ የምድብ ጨዋታ ነገ (ዓርብ ጳጉሜን 3) ከምሽቱ 1:00 ሰዓት ላይ ካይሮ በሚገኘው ጁን 30 ስታዲየም ይካሄዳል።

ጨዋታውን ጋቦናዊ የመሐል ዳኛ እንዲሁም ረዳቶች ከኮንጎ እና ጋቦን የሚመሩት ይሆናል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Back To Top