ቤንች ሸኮ የሙዝ ደን

በቤንች ሸኮ ዞን  ከፍራፍሬዎች ያንበሳውን ድርሻ በመያዝ ግንባር ቀደም የሆነውና ከበቆሎ ምርትና ቡና ምርት በተከታይነት 3ኛ ደረጃን የተጎናፀፈው የሙዝ ተክላችን

የሙዝ ተክል ለመጀመርያ ጊዜ ወደ ሀገራችን የገባው በ1946 ዓ.ም ከኬንያ በሚሽነሪዎችና በቤተክርስቲያን ሰዎች አማካኝነተ እንደሆነ ይነገራል፡፡

ይህ የሙዝ ዝርያ አሁም ካለው ሙዝ ሲነፃጸር ቁመቱ እና ፍሬው አጭር የሆነ የኬንያ ሙዝ የሚባል ነበር፡፡

ይህ የኬንያ ሙዝ በ1972 ዓ.ም ወደ ሚዛን ተፈሪ በበበቃ እርሻ ልማት አማካኝነት ለመጀመርያ ጊዜ ወደ አካባቢያችን (በዞናችን) ሊገኝ እንደተቻለ የቤንች ሸኮ ዞን ግብርና አካባቢ ጥበቃና ህብረት ሥራ መምሪያ ኃላፊ አቶ መስፍን ጉብላ ይገልፃሉ፡፡

የሙዙ ምርት ዘርፈ ብዙ ጥቅሞች አሉት ይላሉ አቶ መስፍን፡፡

ግንዱ ለከብቶች መኖ ይውላል በተጨማሪ ይህን ለከብቶች መኖ የሚውል የሙዝ ግንድ አፈር ውስጥ ሲጣል ለአፈር ለምነት ይጠቅማል የሙዙ ቅጠል ለጎጆ ቤት ክዳን በመሆን በሳር ቦታ ያገለግላል፡፡

እንዲሁም ቅጠሉ ጋር ያለውን ግንድ በልኩ ፀሐይ ብረሀን በማሞቅ ለገመድ ያውሉት ነበር፡፡

ሙዝ ወደ ዋና ተግባሩ ስንሄድ የካርቦ ሃይድሬት ምንጭ ከመሆኑ ጋር በተጨማሪ ቫይታሚን ኤ.ቢ.ሲ ከምግብነቱ እናገኛለን ካሳባ፣ድንች፣የብርና የአገዳ ተክሎች ከላይ የተጠቀሱት ንጥረ ነገሮች የሙዝ ያህል መጠን አይገኝባቸውም ፡፡

ከ1988ዓ.ም በፊት አራት አይነት የሙዝ ዝርዮች ብቻ ነበሩ፡-1ኛ ሀበሻ ሙዝ 2ኛነጭ ኬኒያ ሙዝ 3ኛ አጭር ኬንያ ሙዝና ሀበሻ ቀይ ሙዝ ይባሉ ነበር፡፡

እነዚህን የሙዝ ዝርዮች አርሶ አደሩ በቤት አጥር ዙርያና በድንበር አካባቢ በማዝመር ለቤት ውስጥ የምግብ ፍጆታ ይጠቀም ነበር ፡፡

ይህ የሙዝ ዝርያም ብዙጊዜ የሚገኙበት አካባቢም  በሚዛን አጎራባች ቀበሌዎች ብቻ ነበር ሲሉ የቀድሞ አመጣጡት በጥልቅ አብራርተዋል፡፡

አስከትለው  ዛሬ ተሻሽሎ የምታዮው የሙዝ ዝርያ  ምርትና ምርታማነትን ለማሳደግና ዝርያቸውን በአዲስ  ለማስፋፋት እንደዞናችን በእቅድ የተነሳንበት ጊዜው በ1995 ዓ.ም ነበር  የቀድሞ ቤንች ወረዳ ለሁለት ከመከፈሉ በፊት ከጎሞጎፋ ዞን ከአርባ ምንጭ አሁን የአርባ ምንጭ ሙዝ እያልን የምንጠራውን የሙዝ ዝርያ በማምጣት ከዚህ በፊት በነበሩት ቦታ ለመተካት እንቅስቃሴ እንደተደረገ የመምሪያው ሀላፊ አቶ መስፍን ጉብላ ያብራራሉ፡፡

እንቅስቃሴውም በሰዓቱ እነዚያን የአርባ ምንጭ የሙዝ ዝርያዎች በሁለት ችግኝ ጣብያዎች በሞዴል አርሶ አደሮች አማካኝነት ተሰርቶ  እንዲስፋፉ ከተደረገ በኋላ(ኮንሲፌት)አርሶ አደር ከአርሶ አደር እንዲቀባበሉ በማድረግ ዝርያው እንዲስፋፋና በሁሉም ወረዳዎች እንዲዳረስ ማድረግ ተችሏል በማለት በአሁን ወቅት በዞናችን 3ኛ የኢኮኖሚ ሚንጭ ሆኖ የሚታይ ምርት ነው ያለው የመጀመርያው የቡና ምርት  ሁለተኛው ቦቆሎና ሶስተኛው የሙዝ ምርት ሲሆን በአሁኑ ሰአት የሁለተኝነትን ደረጃ የሚጎናፀፍበት ወቅት ላይ ነን ብለዋል፡፡

ታድያ አሁን የምታዩት የሙዝ ተክል ዝርያው መሻሻሉና ምርትና ምርታማነቱ መጨመሩ ብቻ ሳይሆን በመላው ቤንች ሸኮ የዞን ወረዳዎች እንዲዛመትም ተደርጓል ፡፡

እንደ ክልልም ስናይ በክልላእን ከሚገኙ ዞኖች ውስጥ ቤንች ሸኮ ዞን በሙዝ ምርትና ጥራት የመጀመርያውን ደረጃ ይዞ ይገኛል፡፡

እንደዞናችን ያለን ጠቅላላ የሙዝ ሽፋን 500 ሺህ 78.6 ሄ/ር ሲሆን ከጠቅላላ ምርት ሽፋን ምርት የሚሰጥ 31 ሺህ 86.59 ሄ/ር ነው፡፡

በዚህም ጥሩ የሙዝ ሽፋን ያላቸው በቅደም ተከተል ስናያቸው 1ኛ በቡብ ቤንች 13 ቀበሌዎች የሙዝ ክላስተር ሲኖረው ሰ/ቤንች ደግሞ 12 ቀበሌዎች የሙዝ ክላስተር አለው ሌሎች ወረዳዎችም ስናይ 3ኛ ሸኮ ወረዳ 4ኛ ጉራ ፈርዳ 5ኛ ሚዛን አማን 6ኛ ጊዲ ቤንች 7ኛ ሼይ ቤንች ወረዳዎች ናቸው፡፡

በዞናችንም ሆነ  በክልሉ  በኩል በከፍተኛ ደረጃ ጥሩ ዝርያዎችን በበጀት በማስደገፍ ተገዝተው እየተሰራጩ እና የወቅቱ የትኩረት አቅጣጫ በመሆኑ አምራቹ ማህበረሰብ ስለሙዝ ያለው ግንዛቤ የተሸለና አተያይ የተሸለነው ማለት ይቻላል ብለዋል፡፡

በተጨማሪ ደግሞ የሚደረገው ድጋፍና ክትትል ስራ  በተመለከተ የተሸለ መሆኑ በስራ ሂደቱ መታቀፉና ከክልል ጀምሮ እስከ ወረዳ ድረስ የዘርፉ ባለሙያ መኖሩ የተሻለ አድርጎታልይሁን እንጂ እዚህ ላይ ያሉን ቀሪ ስራዎች ቢኖሩ የስልጠና አሰጣጣችን የተሻለ ማድረግ ነው ወደፊት የምናስተካክለውና በእቅድ የተያዘ የቤት ስራችን ነውም ብለዋል፡፡

ደቡብ ቤንችና ሰሜንቤንች የምርጥ ተሞክሮ ስራ ለመስራትም በዝግጅት ላይ እንገኛለን ሲሉም ገልፀዋል፡፡

የሙዝ ምርታችን  ትልቅ የገቢ ጭምር በመሆኑ በተለያዩ የሚዲያ አማራጮች  እንዲታወቅ የማድረግ ጅምር  ስራ እየተሰራ ነው ሲሉ አክለው ተናግረዋል፡፡

አቶ መስፍን ጉብላ እንደተናገሩት ምርቱም እጅግ በጣም ሰፍቷል  በአርሶአደሩም በሴቶችም በወጣቶችም ተመርቷል አርሶ አደራችን 6 ሄ/ክታርም 5 ሄ/ክታርም አምርቷል።ቨየሙዝ ተክል በእግር የሚቆጠር ምርት ያለው አርሶ አደር አለው ብየ አላምንም ሲሉ የምርቱን በብቃት መመረቱን ይገልፃሉ ፡፡

እንደሀገር እርሶ አደራችን የሙዝ አያያዝና አመራረት የተረዳበት ሁኔታ ላይ ደርሰናልም ብለዋል፡፡

እንግዲህ ይህ የሙዝ ምርት ትልቁ የአርሶ አደሮች የገቢ ምንጭ እየሆነ መጥቷል ከ90%በላይ የዞናችን ማህበረሰብ  በሙዝ ምርት ተሰማርቷል፡፡

አሁን ባለው ሁኔታ እኔ ትልቁ ስጋቴ ካመረትነው ምርት ግማሹ የደረሰ ሲሆን ገና በግማሹ እንደ አካባቢያችን የገባየ ሁኔታ ዋጋው እየቀነሰ ነው::

እንዲህ የረከሰው በአራቱም አቅጣጫ እየተጫነ ነው ወደ ጋምቤላና  አዲስ አበባ ጭምር እየላክን ባለበት ሲሆን ለቀጣይ ደግሞ በሺ የሚቆጠር ሄክታር የሙዝ ምርት እናስነሳለን የሚቆርጥ የሰለጠነ ሞዴል አርሶ አደር አለን።የሚጭን የተደራጁ ማህበራቶች አሉን ነገር ግን ይህን ምርት የሚቀበለን በቂ የሆነ ትስስር የለንም የሚረከበን ያስፈልገናል።

ችግር ይፈታልን ዘንድ ለክልሉ መንግስትም ለፌደራል መንግስትም አሳውቀናል ሲሉ የችግሩን ጉልህነት አንስተውታል፡፡

ጠንክሮ የሰራው አርሶ አደር በምርቱ ጥሩ ገቢ አግኝቶ ቤተሰቦቹን መምራት እንዲችል ለሀገርም የጥሩ የገቢ ምንጥ ማስገኘት እንድንችል የፕሮሞሽን ስራችን ልይ ጠንክረን መስራት ይጠበቅብናል ሲሉ የቀጣይ አቅጣጫቸውን ተናግረዋል፡፡

ቀጣይ በመካከለኛው ምስራቅና በአውሮፓ  ሀገሮች እንዲታወቅ ጥረት እያደረግን እንገኛለን።

በሀገር ውስጥ በማስተዋወቅ በኩል ሚዲያዎችን አደራ የምለው ቤንች ሸኮ ዞን የሙዝ  ምርት በበቂ ሁኔታ አምርቻለሁ ነገር ግን ገበያ አጣሁ እያለ ነው በማለት የራሳቸውን አስተዋፅኦ እንዲያደርጉልን እንጠይቃለን፡፡

በዘላቂነት ሙዝ ለሚፈልግ በማህበራቶቻችን አማካኝነት እዚያው ድረስ ወስደን ማስረከብ የምንችል መሆኑን እንገልፃለን ሲሉ የዞኑ ግብርና አካባቢ ጥበቃና ህብረት ሥራ መምሪያ ኃላፊ አቶ መስፍን ተናግረዋል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Back To Top