በ2015/16 መኸር በዋናዋና አዝርዕት ሰብሎች 323 ሺህ 294 ሄክታር መሬት በማልማት 7 ሚሊዮን ኩ/ል ምርት ለማምረት እየተሰራ መሆኑን የክልሉ ግብርና ቢሮ አስታወቀ፡፡

በ2015/16 መኸር በዋናዋና አዝርዕት ሰብሎች 323 ሺህ 294 ሄክታር መሬት በማልማት 7 ሚሊዮን ኩ/ል ምርት ለማምረት እየተሰራ መሆኑን የክልሉ ግብርና ቢሮ አስታወቀ፡፡

በክልሉ እስካሁን 198 ሺህ 765 ሄ/ር ወይም 61በነጥብ 4 ከመቶ ማሳ በዘር መሸፈኑንም ቢሮው አስታውቋል፡፡

የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድርና የግብርና ቢሮ ኃላፊ አቶ ማስረሻ በላቸው በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ምርታማነቱን ከአምና ተመሳሳይ ወቅት በአማካይ 20 ኩንታል በሄክታር ከነበረበት ወደ 22 ኩንታል በሄክታር በማድረስ 7 ሚሊዮን ኩንታል ምርት ለማምረት የሚያስችል ስራ እየተሰራ ነው ብለዋል፡፡

እስካሁን መታረስ ካለበት 323 ሺህ 294 ሄክታር ማሳ ዉስጥ 318 ሺህ 113 ሄክታር 98.3 ከመቶ ማሳ የተዘጋጀ መሆኑንና ከታረሰዉ ማሳ ዉስጥ 9 ሺህ 453 ሄክታር ማሳ በትራክተር እንዲታገዝ ተደርጓል ሲሉም ተናግረዋል፡፡

በክልሉ 85 ሺህ 724 ሄክታር መሬት በኩታ ገጠም እርሻ ለማምረት ታቅዶ እስካሁን ባለዉ መረጃ 64 ሺህ 567 ሄክታር ማሳ በኩታ ገጠም መዘጋጀቱንና 35 ሺህ 675 ሄክታር ማሳ በዘር መሸፈኑን አቶ ማስረሻ በላቸው ተናግረዋል፡፡

እስካሁን ባለው ምርትና ምርታማነትን ለማሳደግ 17 ሺህ 225 ኩንታል ቅይጥ የአፈር ማዳበሪያ ፣ 1 ሺህ 267 ኩንታል ዩሪያ በድምሩ 18 ሺህ 459 ኩንታል እንዲሁም 5 ሺህ 796 ሳቼት ሕያዉ ማዳበሪያና 11,187 ኩ/ል ምርጥ ዘር ጥቅም ላይ ዉሏል ብለዋል፡፡

በአብዛኛዉ የክልሉ የእርሻ ስራ እያለቀ ቢሆንም አብዛኛዉ ሰብል ተዘርቶ እንዳይጠናቀቅ የመኸር ዝናብ ስርጭት የተዛባ ከመሆኑ የተነሳ በአንዳንድ የክልሉ አካባቢዎች ዘር ሊዘገይ ችሏል ብለዋል፡፡

አብዛኛዉ ማሳ ለዘር መዘጋጀቱንና የዝናቡ ሁኔታ እየታየ ተዘርቶ እንዲጠናቀቅ በቅርበት በግብርና ባለሙያ ድጋፍና ክትትል እየተደረገ ይገኛል ሲሉም ገልጸዋል፡፡

እንደ ክልል ከሸካ ዞን ዉጪ ባሉት የካፋ፣ዳዉሮ፣ቤንችሸኮ፣ምዕራብ ኦሞና ኮንታ ዞኖች የመኸር ዝናብ የመጠን ማነስ ለዘር በቂ ያለመሆን፣ የስርጭት መዛባት እና ጨርሶ መጥፋት በመከሰቱ ምክንያት ዘር በወቅቱ ለመዝራት አርሶ አደሩ ከመቸገሩም ባለፈ ተዘርቶ የበቀለ የሰብል ቡቃያ በቆላማ አከባቢዎች እየደረቀ እንደሆነም ማረጋገጥ መቻሉንም ጠቁመዋል።

አቶ ማስረሻ በላቸው የችግሩን መጠን ለመለየት ድጋፍ ሰጪ ቡድን ተዋቅሮ በሁሉም ዞኖች መውረዱን ተናግረዋል፡፡

አሁን ላይ ያለው የዝናብ ስርጭት ሁኔታ መሻሻል ካሳየ አርሶ አደሩ ዘር መልሶ እንዲዘራ የማድረግ ስራ እንደሚሰራ የተናገሩት አቶ ማስረሻ ችግሩ ተባብሶ የሚቀጥል ከሆነም ከክልሉ አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን ጋር ችግሩን ለመቅረፍ የቅድመ ዝግጅት ስራዎች እየተሰሩ መሆኑን ተናግረዋል።

southwestcommunication

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Back To Top