በክልላችን የሚገኙ የተፈጥሮ ጸጋዎችን ወደ ሀብት በመቀየር ወጣቶችን ተጠቃሚ ማድረግ ያስፈልጋል ፦ ክቡር አቶ ፋጂዮ ሳፒ

በክልላችን የሚገኙ የተፈጥሮ ጸጋዎችን ወደ ሀብት በመቀየር ወጣቶችን ተጠቃሚ ማድረግ ያስፈልጋል ፦ ክቡር አቶ ፋጂዮ ሳፒ

ሚዛን አማን ፣ ጳጉሜ 01/2015 የክልሉ ኢንተርፕራይዝና ኢንዱስትሪ ልማት ቢሮ ከደች ሲኖ የምስራቅ አፍሪካ የቀርቀሀ ልማት ፕሮግራም 2 ጋር በመተባበር ለ10 ቀናት የሰጠው ስልጠና ተጠናቋል።

በምክትል ርዕሰ መስተዳድር ማዕረግ የኢኮኖሚ ክላስተር አስተባባሪና የክልሉ ትራንስፖርትና መንገድ ልማት ቢሮ ኃላፊ አቶ ፋጂዮ ሳፒ በመድረኩ ባደረጉት ንግግር ቀርቀሀ እንደ ቻይና ባሉ ሀገራት የማኑፋክቸሪንግ ዘርፉ ትልቅ ግብዓትና ለበርካታ የሀገሪቱ ዜጎች የስራ ዕድል የፈጠረ ነው ብለዋል።

እንደ ደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ቀርቀሀ በተለያዩ አካባቢዎች በስፋት ቢገኝም በዘርፉ የሰለጠነ የሰው ሀይልና አለመኖሩና እንደ አማራጭ የኢኮኖሚ ምንጭ ተደርጎ አለመወሰዱ ምርቱ ጥቅም ሳይሰጥ ቆይቷል ብለዋል። በቅርቡ በክልሉ የተለያዩ አካባቢዎች ለወጣቶች በዘርፉ ስልጠና እየተሰጠ መሆኑን ገልጸው ሰልጣኞችም ሙያውን በማሻገር የኢኮኖሚ ምንጭ ሊያደርጉ ይገባል ብለዋል።

የክልሉ ኢንተርፕራይዝና ኢንዱስትሪ ልማት ቢሮ ኃላፊ አቶ ግዛው ጋጊያብ በበኩላቸው የስራ ዕድል ፈጠራ ስራ በባህሪው የበርካታ ባለድርሻ አካላትን ድጋፍና ርብርብ የሚጠይቅ ነው ብለዋል። በዚህም ከአምና ጀምሮ ከፌደራል ባህልና ቱሪዝም ሚንስቴር ፣ ከክልሉ ባህል ቱሪዝምና ስፖርት ቢሮና አጋር ድርጅቶች ጋር በመቀናጀት ለወጣቶች በተለያዩ የሙያ መስኮች አጫጭር ስልጠናዎች እደተሰጡ ነው ብለዋል።

በተያዘው በጀት አመትም በተለያዩ የሙያ መስኮች ወጣቶችን በማሰልጠን የሙያ ባለቤት ለማድረግ መታቀዱን ገልጸው የዚሁ አካል የሆነው በቀርቀሀ ተክል የዕደ ጥበብ ስራ ላይ ከቤንች ሸኮና ከሸካ ዞን ለተውጣጡ 30 ወጣቶች ለ10 ቀናት በሚዛን ግብርና ቴክኒክና ሙያ ትምህርት ስልጠና ኮሌጅ በንድፈ ሀሳብና በተግባር የተደገፈ ስልጠና ተሰጥቷል ብለዋል።

የሚዛን ግብርና ቴክኒክና ሙያ ትምህርት ስልጠና ኮሌጅ ዲን አቶ ሀብታሙ ካፍቲን በመድረኩ ተሞክሯቸውን ሲያካፍሉ እንደተናገሩት ቀርቀሀ በሀገረ ቻይና ምግብ ፣ ልብስ ፣ መጠለያ ፣ የቤት ቁሳቁስ ፣ የፋብሪካ ውጤትና በአጠቃላይ ከህዝቡ ህይወትና ኢኮኖሚ ጋር እጅግ የተቆራኘ ነው ብለዋል።

እንደ ደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ አብዛኛው ለቤትና ለቢሮ ቁሳቁስ መስሪያነት ሀገር በቀል የደን ውጤቶችን በመጨፍጨፍ መሆኑን ጠቁመው ይህም ለአየር ንብረት ለውጥና ለተፈጥሮ አደጋዎችን ተጋላጭ እያደረገን ይገኛል ብለዋል። ቀርቀሀን አማራጭ የማኑፋክቸሪንግ ውጤት ማድረግ ያስፈልጋል ያሉት ዲኑ በዚህ ዘርፍ ከሚሰሩ አካላት ጋር በጋራ ለመስራት ዝግጁ መሆናቸውን ገልጸዋል።

በመድረኩ በሰልጣኞች የተሰሩ የእደ ጥበብ ውጤቶች ጉብኝት የተደረገ ሲሆን ለሰልጣኞች በዕለቱ እንግዳ የምስክር ወረቀት ከእለቱ የክብር እንግዳ እጅ ተቀብለዋል።

በመጨረሻም የክልሉ ኢንተርፕራይዝና ኢንዱስትሪ ልማት ቢሮ ከሚዛን ግብርና ቴክኒክና ሙያ ትምህርት ስልጠና ኮሌጅ ጋር በቀጣይ አመታት በጋራ ለመስራት የሚያስችላቸውን የመግባቢያ ሰነድ ተፈራርመዋል።

በተዘራ ጥላሁን

ለበለጠ መረጃ ፦
ድረ ገጽ፦ www.benchshekozonecom.gov.et
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/benchshekozonepublicrelationoffice
ዩትዩብ፦ https://youtube.com/@BenchShekoZoneGovernmentCommun?feature=share8
ቴሌግራም፦ https://t.me/bszgca
ትዊተር፦ https://twitter.com/BenchGov?t=V1DGL3YnPHirGEiTq-jh2A&s=09
ኢንስታግራም፦ https://instagram.com/benchshekozonepr?utm_source=qr&igshid=MzNlNGNkZWQ4Mg%3D%3D
ቲክቶክ፦ tiktok.com/@benchshekozonegov
በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Back To Top