በክልሉ አንድ የተቀናጀ እና የሚናበብ የኮሙኒኬሽን ቤተሰብ በመፍጠር የተግባቦት ሥራን ውጤታማ ማድረግ ይቻላል:-አቶ የሺዋስ ዓለሙ

በክልሉ አንድ የተቀናጀ እና የሚናበብ የኮሙኒኬሽን ቤተሰብ በመፍጠር የተግባቦት ሥራን ውጤታማ ማድረግ ይቻላል:-አቶ የሺዋስ ዓለሙ

የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልላዊ መንግስት የመንግሥት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ ውጤታማ ተግባቦት የመፍጠር አስፈላጊነት በሚል መርህ ሃሳብ ለሚዲያ እና ኮሙዩኒኬሽን አመራሮችና ባለሙያዎች የተዘጋጀ የፓናል ውይይት መድረክ ተጀምሯል ፡፡

በምክክር መድረኩ የክልሉ የመንግሥት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ ኃላፊ አቶ የሺዋስ ዓለሙ እንደገለፁት በ2015 በጀት ዓመት በክልሉ የሚገኙ የሚዲያ እና ኮሙኒኬሽን ሴክተር በማስተባበር በርካታ ውጤታማ ስራ መሰራቱን ገልጸዋል።

አቶ የሺዋስ አክለውም በክልሉ አንድ የተቀናጀ እና የሚናበብ የኮሙኒኬሽኑን ቤተሰብ በመፍጠር የተግባቦት ሥራን ውጤታማ ማድረግ ይቻላል ብለዋል።

ከዚህም መነሻ በክልላችን ውጤታማ ተግባቦት ለመፍጠር እንዲያስችል በክልሉ ውስጥ ለሚገኙ ለሚዲያ እና ኮሙዩኒኬሽን አመራሮችና ባለሙያዎች የፓናል ውይይት መድረክ ተዘጋጅቷል ብለዋል።

መድረኩ ውጤታማ ተግባቦት ለመፍጠር በተዘጋጀው ሰነድ ላይ ዉይይት እንደሚያደርግም አቶ የሺዋስ ገልጸዋል።

በመድረኩ የቢሮው ሎጎና ድረ-ገፅ የማስተዋወቅ ሥራ ተሰርቷል።

በምክክር መድረኩ የክልሉ ምክር ቤት ምክትል አፈጉባኤ ወ/ሮ ፀሀይ ዳርጫና የርዕሰ መስተዳድሩ የመልካም አስተዳደር ጉዳዮች አማካሪ አቶ አክሊሉ ከበደን ጨምሮ የክልል፣ የዞንና የከተማ አስተዳደር የሚዲያ አመራሮች እና ባለሙያዎች እየተሳተፉ ነዉ።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Back To Top