በከተማው የታየው የትምህርት ቤት ደረጃ ማሻሻል ስራ ተጠናክሮ ሊቀጥል እንደሚገባ ተገለፀ።

በከተማው የታየው የትምህርት ቤት ደረጃ ማሻሻል ስራ ተጠናክሮ ሊቀጥል እንደሚገባ ተገለፀ።

ሚዛን አማን ነሃሴ 21/2015 ዓ.ም ትምህርት ለትውልድ በሚል መርህ የትምህርት ቤቶችን ደረጃ ለማሻሻልና የ2016 ዓ.ም ትምህርት ለማስጀመር እየተሰሩ ያሉ ስራዎችን በተመለከተ በሚዛን ቁጥር አንድ ትምህርት ቤት ውይይት ተደርጓል።

በውይይቱ ላይ የተገኙት የሚዛን አማን ከተማ ከንቲባ አቶ ግሩም ተማም እንደገለጹት በሚዛን ቁጥር አንድ ትምህርት ቤት የታየውን መነሳሳት በሌሎችም ትምህርት ቤቶች ልንደግመው ይገባል ብለዋል።

ከንቲባው አክለውም ተግባሩ የፈረሱ ትምህርት ቤቶችን ከመገንባት በተጨማሪ አንድነታችንን እንድንገነባና እንድንቀራረብ አድርጎናል ብለዋል።

በውይይቱ በሚዛን ቁጥር አንድ ትምህርት ቤት መንግስታዊ መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች፣ ባለሃብቶች፣ የቀድሞ የትምህርት ቤቱ ተማሪዎችና በውጪም በሃገር ውስጥም የሚገኙ ግለሰቦች ባደረጉት ርብርብ ቃል ከተገባው ውጪ ከ607 ሺህ 535 ብር በላይ መሰብሰቡና በአይነት ከ148 ሺህ 250 ብር የሚገመት ድጋፍ ተደርጎ በርካታ ስራዎች እየተሰሩ መሆናቸው ተጠቅሷል።

ግቢውን ለተማሪዎች ምቹ ለማድረግ የሚዛን አማን ከተማ አስተዳደር ዋና ማዘጋጃ ቤት ባደረገው የሎደር ድጋፍ የትምህርት ቤቱን ግቢ የመደልደል ስራ እየተሰራ መሆኑና ግቢውን ኮረት ለማልበስ የሚመለከታቸው አካላት ድጋፋቸውን አጠናክረው እንዲቀጥሉ ጥሪ ቀርቧል።

ትምህርት ቤቱን ምቹ ማድረግና የ2016 ትምህርትን ለማስጀመር ግለሰቦች ወንበሮችን በመጠገን፣ ክፍሎችን ቀለም በመቀባትና ጅብሰም በማልበስ፣ የክፍሎችን ጣሪያ ቀለም በመቀባት ከፍተኛ ርብርብ እየተደረገ መሆኑ ተገልጿል።

አቶ ተስፋ ታደሰ የቀድሞ የትምህርት ቤቱ ተማሪ ሲሆኑ በድርጅታቸው የማሰሩ ሰራተኞችን ለትምህርት ቤቱ በመመደብ በርካታ የብረት ወንበሮችን እያስጠገኑ መሆናቸውንና ይህም በገንዘብ ሲተመን ከ70 እስከ 80 ሺህ ብር የሚያወጣ ስራ እየሰሩ መሆናቸውን ገልጸውልናል።

በተመሳሳይ በሚዛን 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት 169 ሺህ ብር ቃል ከተገባው 82 ሺህ ብር ገቢ መደረጉና በዚህም ስራዎች እየተሰሩ መሆናቸው ተመላክቷል።

በትምህርት ቤቶቹ ሃብታቸውን፣ ጊዜያቸውን፣ ጉልበታቸውንና ሃሳባቸውን እያዋጡ ያሉ በርካታ የህብረሰብ ክፍሎች መኖራቸውና ከሰዎች የተገኘው ሃብትም ሳይውል ሳያድር ስራ ላይ እየዋለ መሆኑ ተጠቅሷል።

የትምህርት ቤቶችን ደረጃ ለማሻሻል የማሰራው ስራ ተጠናክሮ መቀጠል እንዳለበት የተገለጸ ሲሆን በሚዛን አማን እየተሰራ ያለው ስራ በርካታ ለውጦች የታዩበትና ከፍተኛ የአመራር ቁርጠኝነት የታዬበት በመሆኑ ለሌሎች አካባቢዎች ተሞክሮ ሊሆን የሚችል መሆኑም ተጠቅሷል።

የትምህርት ቤቱን ደረጃ ለማሻሻልና ደረጃውን የጠበቀ ህንጻ ለማሰራት በሚዛን ቁጥር አንድና በሚዛን ሃይስኩል ስራዎችን የሚሰራ 9 ዓባላት ያለው ኮሚቴ መዋቀሩ ተነግሯል።

ኮሚቴው በሁለቱ ትምህርት ቤቶች ላይ ሃብት በማሰባሰብ፣ እቅዶችን በማቀድ፣ ሰዎችን በማስተባበር ሰፊ ስራ የሚሰራና ሃላፊነቱን በተገቢው የሚወጣ መሆኑም ተጠቅሷል። የከተማው መንግስት ኮሙኒኬሽን ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Back To Top