በንፁ የመጠጥ ውሃ የበለፀገ ዞን ለመፍጠር ተግተን እንሰራለን

ውሃ በዓለማችን ላይ በእጅጉ ለሕይወት አስፈላጊ ከሆኑት ንጥረነገሮች ዋነኛው ነው።

ውሃ ለሰው ልጅ እጅግ ጠቃሚ ነው። የሰውነታችንን ሁለት ሶስተኛ ክብደትንም ይይዛል፣ ሰውነታችን ውስጥ ያሉ ንጥረ ነገሮችና አላሰፈላጊ ቆሻሻዎችን ያጓጉዛል፣ የሰውነታችንን ሙቀት ይቆጣጠራል፣ ሰውነታችን እንዲለሰልስና መገጣጠሚያዎቻችን ላይ የሚፈጠርን መጎርበጥ እንዲቀንስ ያደርጋል፣ ሰውነታችን ውስጥ የሚካሄድ የኬሚካል ውህደትን ያግዛል።

ሰዎች ተፈጥሮአዊ እንቅስቃሴዎችን ሲያደርጉ በላብ፣ በሽንትና በትንፋሽ በኩል ሰውነታቸው ውስጥ ያለው ውሃ እየቀነሰ ይሄዳል። በሰውነታችን ውስጥ በቂ የውሃ ክምችት እንዳለን ማረጋገጥ ድርቀትን ለመከላከል ወሳኝ ነው።

ከ1-2 በመቶ የሰውነታችንን የውሃ መጠን ስናጣ ድርቀት እንደሚያጋጥመን ይታወቃል። የድርቀት ምልክቶችን ማወቅ ቀላል ነው፤ ሰውነታችን እንደገና ፈሳሽ እሰከሚያገኝ ድረስ ድርቀቱ እየተባባሰ ሊሄድ ይችላል። የተለመደ ነገር ባይሆንም ድርቀት ለሞት እስከማብቃትም ሊያደርስ ይችላል።

ለዞኑ ህዘብ የንፁህ  መጠጥ ውሃን ተደራሽ ለማደረግ በትኩረት  እየተሰራ  መሆኑን  የቤንች ሸኮ ዞን ውሃ ማዕድን ኢነርጂ መምሪያ ኣአስታውቋል።

 በዞኑ ባለፉት 9(ዘጠኝ )ወራት የንፁህ መጠጥ ውሃ ለህዝቡ ተደራሽ  ለማደረግ በረካታ  ተግባራት ተከናውነዋል ይላሉ ሀላፊው።

በዚህም ከ5.9 ሚሊዮን ብር በላይ በሆነው ወጪ የንፁህ መጠጥ ውሃ ተቋማት ግንባታ ሰራ በህብረተሰብ ተሳትፎ ማከናወን መቻላቸውንም  ሀላፊው አስታውቀዋል።

የመምሪያው  ሀላፊ አቶ ወልደየስ     ዘለቀ  እንደገለፁት የዞኑ ንፁህ  መጠጥ ውሃ ሸፋን ከነበረበት 34.7 ፐርሰንት ወደ 35.9 ፐርሰንት ለማሳደግ ልዩ ትኩረት  እየተሰራ እንደሚገኙም ተናግረዋል።

የዞኑን ለህዝብ የንፁህ  መጠጥ ውሃን ተደራሽ ለማድረግ መንግስት እና መንግታዊ ካለሆኑት ድርጀቶች ጋራ በማቀናጀት የምንጭ ግንባታ እና የጥልቅ ወሃ  ቆፋሮ ስራዎች በሁለቱም ወረዳዎችና ከተማ አሰተዳደሮች እየተሰራ እንደሚገኝ  ሀላፊ ው አሰረድተዋል

በዚህም  በያዝነው  በጀት  አመት ባለፋት 9 ወራትም  5 ሚሊዮን 980 ሺ ብር  በላይ በሆኑ ውጪ  54 የንፁህ መጠጥ ውሃ የምንጭ ግንባታ ሰራዎች በህብረተሰቡን  ተሳትፎ እየተሰራ ሲሆን  ከእነዚህ  ውሰጥ 32 የንፁህ  መጠጥ ውሃ የምንጭ  ግንባታ   ሰራ  በማጠናቀቅ ቀሪዎቹን  ለማጠናቀቅ በትኩረት  እየተሰራ   መሆኑን  ገለፀዋል ።

በቁጥር 12 ከፈተኛ የሚሆኑ የጥልቅ ውሃ ጥናትና ዲዛይን ሰራ ለመስራት  ታቅዶ 11 የጥልቅ  ውሃ ጥናትና ዲዛይን እየተሰራ ሲሆን 4 የእጅ  ፓምኘ ውሃ ጥናትና  ዲዛይን ሰራ ለመስራት  እንዲሁም  ታቅዶ 4ቱ መከናወኑን  መቻሉን  ሀላፊው  ተናገረዋል ።

የ3 ነባር የመጠጥ ወሃ ተቋማት የማስፋፊያ ጥናት  ማካሄድ  ታቅዶ  በ2ቱ የመጠጥ ውሃ ተቋማት ማስፋፊያ  ሰራ መከናወኑን መቻሉን  ሀላፊው  ገልፆው የወሃ ጥራት ላብራቶሪ ምርመራ በ14 የመጠጥ ውሃ ተቋማት ላይ በውሃ ጥራት የላብራቶሪ ናሙና ምርመራ ለማደረግ  ታቅዶ በ12 የመጠጥ ወሃ ተቋማት ላይ ባይሎጃካል የውሃ ጥናት የላብራቶሪ ምርመራ ማድረግ  መቻሉን  ገልፀዋል ።

የንፁህ  መጠጥ ውሃ ምንጮች  ግንባታም  እየተከናውኑ አካባቢዎች በሰ/ቤንች ፥ በደ/ቤንች፥ በሼ/ቤንች ፥በጊ/ቤንች፥በሸኮእና ጉራፈርዳ  ወረዳዎች መሆናቸውንም  አቶ ወልደየስ  ገለፀው የገጠሩ  ህዝብ ንፁህ  መጠጥ ውሃ ተደራሸ ለማድረግ  እየተሰራ  መሆኑን  አሰረድተዋል ።

 በተለይ ጥልቅ ውሃ ተቋማት ግንባታ ውሰጥ የተሻለ አፈፃፀም እየተመዘገበበት ካሉት የሸኮ ወረዳ ቦታ ቀበሌ የንፁህ  መጠጥ ውሃ እና የግዝመሬት ሺሚ ቀበሌዎች የንፁህ  መጠጥ ውሃ ግንባታ ስራዎች የተሻለ  ተጠቃሽ መሆኑን የተናገረው አቶ ወልደየስ የሼ/ቤንች ወረዳ ማዝ ቀበሌ የንፁህ  መጠጥ ውሃ  ግንባታ  የተወሰነ  ችግሮች  በመኖራቸው  ችግሮችን ለመፈታት እየተሰራ እንደሚገኝ አሰረድተዋል ።

በአጠቃላይ  በዞን ደረጃ 1284 የንፁህ መጠጥ ውሃ ተቋማት የሚገኙ  ሲሆን 1189 የንፁህ የመጠጥ የውሃ  ተቋማት በገጠር  አካባቢ  የሚገኙ  ሲሆን  95ቱ የከተማ   የንፁህ  መጠጥ ውሃ የተቋማት  መሆናቸውንም  አቶ ወልደየስ  ተናገረው  ከእነዚህ  ውሰጥ 983 የንፁህ  መጠጥ ውሃ ተቋማት  አገልግሎት የሚሰጡ ሲሆኑ ቀሪው 301 የሚሆኑ  የንፁህ መጠጥ የውሃ ተቋማት አገልግሎት  የማይሰጥ  መሆናቸውንም አስገንዝበዋል ።

ሀላፊው  አያይዘውም  እየተገነቡ  ያለው የንፁህ መጠጥ የውሃ ተቋማት  ህብረተሰቡ  በጥንቃቄ  በመያዝ  መጠቀም  እንዳለባቸው  ተናገረው ህብረተሰቡን የንፁህ  መጠጥ ውሃ  ተቋማት  ከብክነትን በመጠበቅ  መጠቀም  እንዳለባቸው ሀላፊው አስገንዝበዋል ።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Back To Top