በተያያዘ በጀት አመት በክልሉ ለ128ሺ ወጣቶች የስራ ዕድል ለመፍጠር እየተሰራ መሆኑ ተገለጸ።

በተያያዘ በጀት አመት በክልሉ ለ128ሺ ወጣቶች የስራ ዕድል ለመፍጠር እየተሰራ መሆኑ ተገለጸ።

ሚዛን አማን ፣ ነሀሴ 17/2015 የክልሉ ኢንተርፕራይዝና ኢንዱስትሪ ልማት ቢሮ የስራ ኃላፊዎች ከዞንና ከሚዛን አማን ከተማ አስተዳደር አመራሮች ጋር የማምረቻ ሼዶችን የስራ እንቅስቃሴ ተዘዋውረው ምልከታ አድርገዋል።

በቤንች ሸኮ ዞን በሚዛን አማን ከተማ አስተዳደር በክልሉ መንግስት ተገንብተው ወደ ስራ የገቡ የማኑፋክቸሪንግ የማምረቻ ሼዶች የስራ እንቅስቃሴ በክልል ፣ በዞንና በከተማ አስተዳደሩ የስራ ኃላፊዎች ጉብኝትና ምልከታ ተደርጓል።

በሚዛን ከተማ በቄቀር አካባቢ የሚገኘው የምግብና ምግብ ነክ ማምረቻ ሼድ እንዲሁም በአማን ከተማ የእንጨትና ብረታ ብረት ፣ የሚስማርና የችፑድ ማምረቻ ሼዶች የጉብኝቱ አካል መሆን ችለዋል።

የክልሉ ኢንተርፕራይዝና ኢንዱስትሪ ልማት ቢሮ ኃላፊ አቶ ግዛው ጋጊያብ እንደተናገሩት በተያዘው በጀት አመት በክልሉ ለ128ሺ ወጣቶች የስራ ዕድል ለመፍጠር እየተሰራ መሆኑን ተናግረዋል።ከምዕራብ ኦሞ ዞን በስተቀር በክልሉ ሁሉም ዞኖች የማምረቻ ሼዶች ተገንብተው ወደ ስራ መግባታቸው ገልጸዋል።

በምልከታው የውጭ ሀገር ቴክኖሎጂዎችን በመቅዳትና በሀገር ምርት በመተካት ውጤታማና እንደ ክልል ተሞክሮ ሊሆን በሚችል መልኩ ቤንች ሸኮ ዞን ላይ በኢንተረፕራይዞች ውጤታማ ተግባራት መሰራታቸውን ተመልክተናል ብለዋል። ይሁን እንጂ በሸካና ቤንች ሸኮ ዞን የሀይል እጥረት መኖሩ በቅሬታ የቀረበ ሲሆን ችግሩን ለመፍታት ከመብራት ኃይል ጋር ውይድት እየተደረገ መሆኑን ኃላፊው ገልጸዋል።

የቤንች ሸኮ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ቀበሌ መንገሻ በበኩላቸው በሚዛን አማን በሚገኙ ሁለት ክላስተሮች ላይ ምልከታ መደረጉን ገልጸው እንደ ሀገር ሞዴል የሚሆኑ ስራዎችን መመልከታቸውን ገልጸዋል። በተለይ በአማን ክላስተር ለሌሎች አካባቢዎችና ኢንተርፕራይዞች ተሞክሮ ሊሆን በሚችል መልኩ የውጭ ምንዛሬን የሚያስቀሩና በሀገር ውስጥ ምርት በመተካት ሞዴል ተግባራት ተፈጽመዋል ብለዋል።

በምርት ረገድም ጥራትና ምቾት ያላቸው ከውጭ ከሚገቡ ተመሳሳይ ምርቶች የማይተናነሱ የእንጨትና የብረታ ብረት ስራ ውጤቶችን አይተናል ብለዋል። የሚስማር ማምረቻው አሁን ያለበትን የፋይናንስ እጥረት ከተፈታ በቅርቡ ወደ ስራ መግባት የሚችል መሆኑን ጠቁመዋል። ኢንተርፕራይዞቹ ለበርካታ ዜጎች በቋሚና ጊዜያዊ የስራ ዕድል መፍጠራቸውም ገልጸዋል።

ይሁን እንጂ የሀይል እጥረትና የመሰረተ ልማት ችግሮቹ በፍጥነት እንዲፈቱ ከክልሉና ከሚመለከታቸው አካላት ጋር የተቀናጀ ስራ በመስራት በፍጥነት እንዲፈታ እንሰራለን ብለዋል።

በተዘራ ጥላሁን

ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/benchshekozonepublicrelationoffice
ዩትዩብ፦ https://youtube.com/@BenchShekoZoneGovernmentCommun?feature=share8
ቴሌግራም፦ https://t.me/bszgca
ትዊተር፦ https://twitter.com/BenchGov?t=V1DGL3YnPHirGEiTq-jh2A&s=09
ኢንስታግራም፦ https://instagram.com/benchshekozonepr?utm_source=qr&igshid=MzNlNGNkZWQ4Mg%3D%3D
ቲክቶክ፦ tiktok.com/@benchshekozonegov
ድረ ገጽ፦ www.benchshekocommunication.gov.et
በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Back To Top