በቤንች ሸኮ ዞን ጉራፈርዳ ወረዳ የተከሰተውን የኩፍኝ በሽታ ለመቆጣጠር የተቀናጀ  ሥራ እየተሰራ መሆኑ  ተገለፀ።

በቤንች ሸኮ ዞን ጉራፈርዳ ወረዳ የተከሰተውን የኩፍኝ በሽታ ለመቆጣጠር የተቀናጀ  ሥራ እየተሰራ መሆኑ  ተገለፀ።

የቤንች ሸኮ ዞን ጤና መምሪያ  ኃላፊ አቶ ኤሊያስ ምናሴ በሰጡት መግለጫ  በጉራፈርዳ ወረዳ የኩፍኝ በሽታ በወረርሽኝ  ደረጃ መከሰቱን ጠቁመው ከ200  በላይ ህፃናትና አዋቂዎች  መጠቃታቸውን ገልፀዋል።

የተከሰተው የኩፍኝ በሽታ መሆን አለመሆኑን  በላብራቶሪ  ለማረጋገጥ ናሙና በመላክ የኩፍኝ በሽታ መሆኑ መረጋገጡን አቶ ኤሊያስ  ተናግረዋል ።

በጉራፈርዳ ወረዳ በ10 ቀበሌዎች  መሰል ምልክቶች  መታየታቸውን እና  በተለይ በ2 ቀበሌዎች  መከሰቱ ተረጋግጧል  ብለዋል።

ከወረዳው መረጃው  ከደረሰ በኃላ የዞኑ ጤና መምሪያ  ሁሉን አቀፍ ድጋፍ  እያደረገ ነው ብለዋል ።

የዞኑና የወረዳ ፈጣን ምላሽ ኮሚቴ ፣የጤና ኤክስቴንሽን  ባለሙያዎች ፣የጤና ጣቢያ ባለሙያዎችበጉራፈርዳ ወረዳ ባሉ ቀበሌዎች  የቤት ለቤት የአሰሳና ቅኝት ሥራ እየሰሩ መሆኑን ጠቁመዋል ።

ከዞኑ መጠባበቂያ መድሀኒቶችን ወደ ወረዳው እንዲሄድ በማድረግ እንዲታከሙ እየተደረገ ነው ሲሉ አቶ ኤሊያስ ገልፀዋል ።

በበሽታው የተጠቁት ከህክምና በኃላ  እያገገሙ መሆኑን ጠቁመው የምግብ እጥረትና የወባም ሆነ የተጓዳኝ በሽታ ያለባቸው ለመቋቋም ስለሚከብዳቸው የምግብ አጥረት ላይም ሆነ ተጓዳኝ በሽታዎች ላይም መስራት ይገባል ብለዋል።

ከዚህ ቀደም በደቡብ ቤንች ወረዳ  የኩፍኝ በሽታ ተከስቶ ወረዳውና ዞኑ ባደረገው ጥረት ሙሉ በሙሉ መቆጣጠር መቻሉን ተናግረዋል ።

የኩፍኝ በሽታ በቫይረስ የሚመጣ የቆዳ ሽፍታና ከፍተኛ የራስ ምታት የሚያስከትል  በሽታው በቀላሉ የሚተላለፍ  በህፃናት  ላይ የሚበረታ ነው ብለዋል።

የኩፍኝ በሽታ በፍጥነት የሚተላለፍ ሲሆን የሚሰራጨውም በኩፍኝ በሽታ የተያዘ ሰው ሲተነፍስ፣ ሲያስል፣ ወይም ሲያስነጥስ እንዲሁም በንክኪ ሊተላለፍ እንደሚችል ገልፀዋል ።

በሽታው ከጉራፈርዳ ባሻገር ወደ ሌሎች ወረዳዎችም እንዳይዛመት ከአጎራባች ዞኖች እና ከክልሉ ጤና ቢሮ ጋር እየተሰራ መሆኑን አቶ ኤሊያስ ጠቁመው ።

በያለለት አሰፋ

ድረ ገጽ፦ www.benchshekozonecom.gov.et
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/benchshekozonepublicrelationoffice
ዩትዩብ፦ https://youtube.com/@BenchShekoZoneGovernmentCommun?feature=share8
ቴሌግራም፦ https://t.me/bszgca
ትዊተር፦ https://twitter.com/BenchGov?t=V1DGL3YnPHirGEiTq-jh2A&s=09 
ኢንስታግራም፦ https://instagram.com/benchshekozonepr?utm_source=qr&igshid=MzNlNGNkZWQ4Mg%3D%3D
ቲክቶክ፦ tiktok.com/@benchshekozonegov
  በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Back To Top