በሥራና ሠራተኛ አገናኝ ኤጀንሲዎች የሚስተዋሉ የአሰራር ችግሮች እና ደላሎች በዘርፉ እያደረጉ ያሉት ተሳትፎ መጎላት ህብረተሰቡን እያስመረረ መሆኑን ተገለጸ፡፡

በሥራና ሠራተኛ አገናኝ ኤጀንሲዎች የሚስተዋሉ የአሰራር ችግሮች እና ደላሎች በዘርፉ እያደረጉ ያሉት ተሳትፎ መጎላት ህብረተሰቡን እያስመረረ መሆኑን ተገለጸ፡፡

ህገ-ወጦች ህግን ተከትለዉ የሚሰሩበትና ህጋዊ ኤጀንሲዎችን በማበረታታት የሚስተዋሉ ችግሮች ለመቅረፍ ትኩረት ተሰጥቶ እየተሰራ መሆኑን የቤንች ሸኮ ዞን የስራ፣ ክህሎት ፣ ኢንተርፕራይዝና ኢንዱስትሪ ልማት መምሪያ አሳሰበ፡፡

በሚዛን አማን ከተማ አስተዳደር ህጋዊ ፍቃድ አዉጥቶ የሚሰሩ ከ75 በላይ የሥራና ሠራተኛ አገናኝ ኤጀንሲዎች አሉ፡፡ በተለያዩ ዘርፎች ሠራተኞችን በማገናኘት የህብረተሰቡን ችግሮች እየቀረፉ ይገኛሉ፡፡

ይሁን እንጂ በርካቶች ህግንና ስርዓቱን ጠብቀዉ እንደሚሰሩ ሁሉ ጥቂት የማይባሉ በህገወጥ መንገድ ስራቸዉን በመከወን ህዝቡን የሚያስመርሩ መኖራቸዉ እሙን ነዉ፡፡ በዚህም ዘርፉ የሴክተሩ ባለድርሻ አካል በመሆኑ በዘርፉ የሚስተዋለዉን ተግዳሮት ለመፍታት ዉይይት አስፈልጓል፡፡

የቤንች ሸኮ ዞን የስራ፣ ክህሎት ፣ ኢንተርፕራይዝና ኢንዱስትሪ ልማት መምሪያ ኃላፊ አቶ ክፍሌ ሽፈራዉ እንዳሉት በከተማችን ዉስጥ ህገ ወጥ የሆነ የሰዉ ዝዉዉር እና ከአሰሪና ሠራተኞች ጋር ተያይዞ የሚፈጸመዉ የስራና ሠራተኛ ቅጥር አፈጻጸም ጉድለት መኖሩ ተናግረዋል፡፡

ኃላፊዉ አክለዉም የስራና ሠራተኛ አገናኝ በአዋጅና በመመሪያ የሚተዳደር ቢሆንም አንዳንድ ኤጀንሲዎች ህግን በመጣስ የሚያደርጉት አካሄድ ህዝባችንን እስመረረ ስለሆነ ሊታረም ይገባል ብለዉ ሠራተኛ ሲያስቀጥሩ ኮሚሽን እስከ 2 ሺህ ብር ከህረተሰቡ መቀበልና ከክልል ዉጪ ሰራተኞችን የማስቀጠር ችግሮች ተስተዉሏል ብለዋል፡፡

ከዚህ ጋር ተያይዞ ሠራተኞች ካስቀጠሩም በኋላ በሶስት ቀናት ዉስጥ ከተቀጠሩበት ቤት ዉል እያቋረጡ እንዲወጡ የሚያደርጉ የስራና ሰራተኛ ኤጀንሲዎች አሉ ያሉት አቶ ክፍሌ የዞኑ መንግስት የህዝቡን የመልካም አስተዳደር ችግሮች ለመፍታት ህገ ወጦች ህግን ተከትለዉ የሚሰሩበትና ህጋዊ ኤጀንሲዎችን በማበረታታት የሚስተዋሉ ችግሮች ለመቅረፍ ትኩረት ተሰጥቶ ይሰራል ብለዋል፡፡

በዉይይቱ ከተሳተፉት መካከል አቶ አሸናፊ ተሻለ ፣ ወ/ሪት ምህረት በቀለ እና አቶ ከተማ ሙስቴት እንዳሉት ሁሉም ስራና ሠራተኛ አገናኝ ኤጀንሲዎች ህግን ተከትለዉ እየሰሩ አለመሆናቸዉን ገልጸዉ በሥራና ሠራተኛ አገናኝ ኤጀንሲዎች የሚስተዋሉ የአሰራር ችግሮች እና ደላሎች በዘርፉ እያደረጉ ያሉት ተሳትፎ መጎላት ህብረተሰቡን እያስመረረ መሆኑን በአስተያየታቸዉ አመላክተዋል ፡፡

ለቀረቡት ጥቄዎችና አስተያቶች የሚመለከታቸዉ ስራ ክፍል ኃላፊዎች ምላሽ ሰጥተዉበታል፡፡

በማጠቃለያም እንዳሉት የህዝባችንን የመልካም ችግር የሆኑትን የጫኝና አዉራጅ ማህበራትንና የስራና ሠራተኛ አገናኝ ኤጀንሲዎች ላይ የሚስተዋሉትን ችግሮች ለመቅረፍ ትኩረት ተደርጎ ስለሚሰራ ህዝቡ ከመንግስት ጎን በመሆን ድጋፍ እንዲያደርግ አሳስበዋል፡፡
በካሳሁን ገ/ሚካኤል

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Back To Top