በህገወጥ መንገድ ሲሸጥ የተገኘ የጦር መሳሪያ መያዙን የጉራፈርዳ ፖሊስ ጽ/ቤት ገለፀ።

በህገወጥ መንገድ ሲሸጥ የተገኘ የጦር መሳሪያ መያዙን የጉራፈርዳ ፖሊስ ጽ/ቤት ገለፀ

በቤንች ሸኮ ዞን በጉራፈርዳ ወረዳ ሶስት የፀጥታ አካላት የተሰወሩ ሲሆን ጥብቅ ክትትል ሲደረግ ቆይቶ የጦር መሳሪያው መያዙን የጉራፈርዳ ፖሊስ ጽ/ቤት ገለፀ።

በደረሰን መረጃ መሰረት በቀን 20/12/2015 በጉራፈርዳ ወረዳ ቢፍቱ 01 ቀበሌ በግምት ከምሽቱ 4:00 ገደማ ሶስት የፀጥታ አካላት መሳሪያ ይዘው ተሰውረዋል የሚል መረጃ በመያዝ ጥብቅ ክትትል በማድረግ ከሰራዊቱ ጋር የነበረን ግለሰብ ከዞን የፀጥታ አካላት ጋር በመቀናጀት በቀን 23/ 12/2015 ሚዛን ዕድገት ቀበሌ ወንጀለኛውን በመያዝ ወደ ጉራፈርዳ ወረዳ በማምጣት ምርመራ ሲደረግ 3/ ሶስት ታጣፊ ክላሽ፣ ዘጠኝ የክላሽ ካርታ፣ 386 የክላሽ ጥይት፣ አንድ የወገብ ትጥቅ፣ የጪስ ቦንብ የተገኘ ሲሆን ቀሪ ያልተገኘ 64 የክላሽ ጥይት አንድ ኤፍ ዋን ቦንብ የጠፋ ሲሆን ቀጣይ ጥብቅ ክትትል በማድረግ የምናሳውቅ ይሆናል በማለት የጉራፈርዳ ወረዳ ፓሊስ አዛዥ ሳጅን አየለ ጁፋ ተናግረዋል።

አክለውም አዛዥ ሳጅን አየለ እንደዚ አፀያፊ ተግባር ሲፈፅሙ ለፀጥታ መደፍረስ ትልቅ መንስኤ እንደሆነ በመግለፅ ማህበረሰቡ እንደዚህ ያለ ተግባር ሲይ ለፀጥታ አካላት ጥቆማ እንድሰጡ ሲሉ መልክታቸውን በማስተላለፍ ድጋፍና ክትትል ላደረጉ ለዞን ፖሊስ ምስጋና በማቅረብ ቀጣይም ድጋፋቸው እንዳይለየን ሲሉ ተናግረዋል።

የዘገበው የጉራፈርዳ ወረዳ መንግስት ኮሙኒኬሽን ጽ/ቤት ነው

/

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Back To Top