ርዕሰ መስተዳድር ዶ/ር ኢንጂነር ነጋሽ ዋጌሾ ከኢፌዲሪ መከላከያ ሠራዊት ማዕከላዊ ዳሎል ዕዝ ከፍተኛ አመራሮች ጋር ዉይይት አደረጉ

የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል መንግስትና የፌደራል ከፍተኛ የፀጥታ አመራሮች በክልሉ የተመዘገበውን ሠላም ወደላቀ ደረጃ ማሸጋገር በሚቻልበት ሁኔታ ላይ ነዉ ዉይይቱ ያተኮረዉ።

በዉይይቱ በክልሉ የተመዘገበውን ሠላም ወደ ላቀ ደረጃ ለማሸጋገር በጋራ መስራት በሚቻልባቸዉ ጉዳዮች ላይ እና ሠላሙን አስጠብቆ ለመቀጠልም የቀጣይ የትኩረት አቅጣጫዎች ላይ ምክክር ተደርጓል:

በክልሉ ያለው የሰላም ሁኔታ ከ አስተማማኝ እየሆነ መምጣቱንና ይህም የፀጥታ መዋቅሩና ህዝቡ በጋራ መስራታቸውን የሚያመላክት መሆኑን በዉይይቱ ተነስቷል።

የኢፌዲሪ መከላከያ ሠራዊት የማዕከላዊ ዳሎል ዕዝ ዋና አዛዥ ሌቴናል ጀነራል ዘውዱ በላይ በአርብቶ አደር አካባቢ አልፎ አልፎ የሚታይ የእርስ በርስ እና ድንበር ተሻጋሪ የከብት ዘረፋ የፀጥታ መዋቀሩ በጀመረው ህብረተሰብ አሣታፊ ውይይት ስራዎች ከታገዘ ሊቀረፍ የሚችልና የክልሉ አሁናዊ ሰላም ለልማትና መልካም አስተዳደር መስፈን መሰረት የጣለ መሆኑን ገልጿል።

የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ርዕሰ መስተዳድር ዶክተር ኢንጂነር ነጋሽ ዋጌሾ፣ የክልሉ የመንግስት ዋና ተጠሪ አቶ ፀጋዬ ማሞ እና ሌሎች የክልሉ አስተባባሪ ኮሚቴ አባላትና የክልሉ ፀጥታ መዋቅር ከፍተኛ፣የዕዙ አመራሮችና የፌደራል ፖሊስ አዛዦች በውይይቱ ተገኝተዋል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Back To Top