ለገቢ አሰባሰብ ስራ ተግዳሮት ሊሆኑ የሚችሉ ችግሮችን በመለየት ለገቢ ዕድገት ሁሉም ኃላፊነት ወስዶ መስራት እንደሚጠበቅ ዶ/ር ኢንጂነር ነጋሽ ዋጌሾ አሳሰቡ ።

ለገቢ አሰባሰብ ስራ ተግዳሮት ሊሆኑ የሚችሉ ችግሮችን በመለየት ለገቢ ዕድገት ሁሉም ኃላፊነት ወስዶ መስራት እንደሚጠበቅ ዶ/ር ኢንጂነር ነጋሽ ዋጌሾ አሳሰቡ ።

የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር ዶ/ር ኢንጂነር ነጋሽ ዋጌሾ ለገቢ አሰባሰብ ስራ ተግዳሮት ሊሆኑ የሚችሉ ችግሮችን በመለየት ለክልሉ ገቢ ዕድገት ሁሉም ኃላፊነት ወስዶ መስራት እንደሚጠበቅ አሳስበዋል ።

ከግብር ግመታና አሰባሰብ ጋር ያሉ ቁልፍ ችግሮችን ለማስተካከል እንደሚሰራ ርዕሰ መስተዳድሩ ገልጸዋል ።

የፊት አመራሩ የገቢን ስራ ኃላፊነት ወስዶ መምራት፣ መደገፍና መገምገም ይገባል ያሉት ዶ/ር ኢንጂነር ነጋሽ ዋጌሾ በግብር እና ታክስ ስራ ላይ በታችኛው መዋቅሮች ላይ ስራዎች መሰራት ይገባሉ ብለዋል።

በክልሉ የገቢ ስራን ለማዘመን ግንዛቤ የመፍጠር፣ መረጃ የማጥራት ስራ እንደሚሰራ ምክትል ርዕሰ መስተደድር አስረድተዋል ።

የክልሉን እምቅ አቅም አሟጦ በመጠቀም የገቢ ዕድገትን ለማሻሻል ሁሉም ባለድርሻ አካላት በተቀናጀ መስራት ያስፈልጋል ሲሉም ተናግረዋል ።

በዘርፉ ባለሙያዎች ዘንድ የሚታዩ የክህሎት ክፍተቶችና የአሰራር ጥሰቶችን ለማረም እንዲሁም ችግሮች ሲከሰቱ ህጋዋና አስተዳደራዊ እርምጃ ለመውሰድ ትኩረት እንደሚሰጥም አብራርተዋል።

ገቢን መሰብሰብ ብቻውን በቂ አይደለም ያሉት ምክትል ርዕሰ መስተዳድሩ የሚሰበሰበውን ገቢ ለታለመለት አለማ ከማዋል ረገድ የሚታዩ የክትትልና የቁጥጥር ስራዎች ክፍተቶች ልታረሙ ይገባል ሲሉም አስገንዝበዋል ።

የመድረኩ ተሳታፊዎች በበኩላቸው፤በክልሉ በሁሉም መዋቅሮች ወጥ የሆነ የግብር ግመታ ስርዓቶችና አሠራሮች ሊዘረጉ እንደሚገባ ጠይቀዋል ።

የግብር ስራዎችን አመራሮች ከመደገፍና ከመምራት አንፃር የተጀመሩ ስራዎች እንዲጠናከሩ ጠይቀዋል ።

ለዘርፉ ከመንግስት ለስራ ማስኬጃ ተብሎ የሚበጀተው በጀት ውስን በመሆኑ ስራውን ለማስከሄድ መቸገራቸውን አስተያየት ሰጪዎች አመልክተዋል ።

በመድረኩ የክልሉ ገቢዎች ቢሮ ኃላፊ ወ/ሮ ህይወት አሰግድ የደረጃ ”ሐ”ዕለት ሽያጭ ጊዜ የተጠናቀቀ መሆኑን በመገንዘብ ያልከፈሉና ግመታ ያልተደረገባቸው ግብር ከፋዮች ላይ አመራሩና የዘርፉ ባለድርሻ አካላት በቅንጅት መስራት አለበት ብለዋል።

የደረሰኝ ቁጥጥር ስራ ለገቢ ቢሮ ብቻ የሚተው ጉዳይ ያለመሆኑን ያነሱት ኃላፊዋ በዚህም የፊት አመራሮች ከተቋሙ ጋር በጋራ እንዲሰሩ ጠይቀዋል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Back To Top