ለዜጎች የሥራ ዕድል ከመፍጠር ባለፍ ስራ ፈጣሪ መሆን እንዲችሉ ዘርፈ ብዙ ስራዎችን እየሠራ እንደሚገኝ የቤንች ሸኮ ዞን የስራ ክህሎት ኢንተርፕራይዞችና ኢንዱስትሪ ልማት መምሪያ አሳወቀ።

ለዜጎች የሥራ ዕድል ከመፍጠር ባለፍ ስራ ፈጣሪ መሆን እንዲችሉ ዘርፈ ብዙ ስራዎችን እየሠራ እንደሚገኝ የቤንች ሸኮ ዞን የስራ ክህሎት ኢንተርፕራይዞችና ኢንዱስትሪ ልማት መምሪያ አሳወቀ።

ሚዛን-አማን፦ነሐሴ 18/2015 ዓ.ም የቤንች ሸኮ ዞን የስራ ክህሎት ኢንተርፕራይዞችና ኢንዱስትሪ ልማት መምሪያ የ2015 ዓ.ም አፈፃፀም ፣የ2016 መሪ ዕቅድ እና የስራ ፈላጊ ወጣቶች ልየታ የንቅናቄ መድረክ ተካሄዷል።

በንቅናቄው መድረክ ተገኝተው መልዕክት ያስተላለፉት የቤንች ሸኮ ዞን ዎና አስተዳዳሪ አቶ ቀበሌ መንገሻ ዘርፉ በዋነኝነት በዞኑ ወጣቶች ላይ ትኩረት አድርጎ የሚሰራና ስራ አጥ የሆኑ ዜጎች ስራ ተፈጥሮላቸው ኑሯቸውን ማሻሻል እንዲችሉ ትኩረት ሰጥቶ የሚሰራ ተቋም ነው ሲሉ ተናግረዎል።

ተቋሙ ለወጣቶች የሥራ ዕድል ከመፍጠር ባለፍ ስራ ፈጣሪ መሆን እንዲችሉ ዘርፈ ብዙ ስራዎችን መስራት እንደሚጠበቅበትም ገልፀዋል። ለዜጎች የስራ ዕድል መፍጠር በመንግሥት ብቻ ሊፈታ የማይቻል መሆኑን ጠቁመው በተለይ የግል ዘርፉ እና ከባለድርሻ አካላት ጋር በመቀናጀት መስራት እንደሚገባ አሳስበዋል ።

አቶ ቀበሌ መንገሻ አክለውም የስራ ዕድል ፈጠራው በአመዛኙ ጊዜያዊ መሆን ፣ በከተማ ግብርና ሥራ ዕድል ፈጠራ ፣ በብድር ስርጭት እና ብድር ማስመለስ ላይ የታዩ ጉድለቶችን በቀጣይ ትኩረት ተሰቶበት እንዲሰራ አስገንዝበዋል።

አቶ ክፍሌ ሽፈራው የቤንች ሸኮ ዞን የስራ ክህሎት ኢንተርፕራይዞችና ኢንዱስትሪ ልማት መምሪ ኃላፊ
በ2016 በጀት ዓመት እንደ ዞን በአጠቃላይ 27ሺ 4 መቶ 95 ስራ አጥ ልየታ ለማደርግ የታቀደ ሲሆን በሚደረገው የሥራ አጥ ልየታና ምዝገባ ላይ ተገቢ ትኩረት መሠጠቱን አንስተዎል።

በተዘዋዋሪ ፈንድ የተሰራጩ የብድር ገንዘቦችን ተከታትሎ አለማስመለስ፣ ከባለድርሻ አካላት ጋር ተቀናጅቶ አለመስራት እና ባለድርሻ አካላት የስራ ዕድል ፈጠራን የራስ ተግባር አድርጎ ያለመስራት በዞኑ ለተለዩ ስራ አጥ ወጣቶች ስራ ለመፍጠር ለሚደረግ ተግባር ተግዳሮት ነው ሲሉ ተናግረዎል።

የኢንተርፕራይዞችን ልማት ለማፋጠንና የስራ አጥ ወጣቶችን ቁጥር ለመቀነስ ትኩረት አድርጎ እየተሰራ እንደሆነም ሀላፊው አሳውቋል።

በመድረኩ በ2015 በጀት ዓመት የተሰሩ ስራዎች ሪፖርት ፣ የ2016 በጀት ዓመት ዕቅድ እና የስራ አጥ ልየታ የንቅናቄ ሰነድ ቀርቦ ሰፋ ያለ ውይይት ተደርጎበታል።

በውይይቱ ከተሳታፊዎች ለተነሳው ጥያቄ ከመድረኩ ምላሽ እና ማብራርያ ተሠቶበት በቀጣይ በሚሰሩ ተግባራት ላይ የጋራ መግባባት ላይ ተደርሷል ።

በእየሩሳሌም አለሙ

ወቅታዊ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ www.benchshekozonecom.gov.et
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/benchshekozonepublicrelationoffice
ዩትዩብ፦ https://youtube.com/@BenchShekoZoneGovernmentCommun?feature=share8
ቴሌግራም፦ https://t.me/bszgca
ትዊተር፦ https://twitter.com/BenchGov?t=V1DGL3YnPHirGEiTq-jh2A&s=09
ኢንስታግራም፦ https://instagram.com/benchshekozonepr?utm_source=qr&igshid=MzNlNGNkZWQ4Mg%3D%3D
ቲክቶክ፦ tiktok.com/@benchshekozonegov
በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Back To Top