ለሰላም ለልማትና ለዴሞራሲ ሲባል የሚከፈል መስዋዕትነትና የሀገርን ህልውና ለማስጠበቅ ብልፅግና ፓርቲ ግምባር ቀደም ተግባሩ አድርጎ ሰርቷል፤ እየሰራም ይገኛል ፡፡ አቶ ዮናስ ኬና

ለሰላም ለልማትና ለዴሞራሲ ሲባል የሚከፈል መስዋዕትነትና የሀገርን ህልውና ለማስጠበቅ ብልፅግና ፓርቲ ግምባር ቀደም ተግባሩ አድርጎ ሰርቷል፤ እየሰራም ይገኛል ፡፡ አቶ ዮናስ ኬና

የቤንች ሸኮ ዞን የመንግስት ዋና ተጠሪና የብልፅግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ሀላፊ አቶ ዮናስ ኬና የመስዋዕትነትን ቀን አስመልክተው መልዕክት አስተላልፈዋል።

የመንግስት ተጠሪው በመልዕክታቸው ፓርቲው የሚከፈለው ዋጋና መስዋዕትነት የሚታሰበውን ሰላምን ለማስፈን: ልማትን ለማረጋገጥና የዴሞራሲን ስርዓት ለማስፋት መሆኑን ገልፀዋል፡፡

ከሁሉም በላይ የሕዝብ ደኅንነትና የአገር ህልውና ጉዳይ ማዕከላዊ ነጥብ ሰላም በመሆኑ፣ የማንኛውም ውሳኔ መነሻና መድረሻ በዚህ ላይ ማጠንጠን ይጠበቅበታል ብለዋል፡፡

ከሕዝብና ከአገር በላይ የሚቀድም አይኖርም ያሉት አቶ ዮናስ ኬና ኢትዮጵያ ከምንጊዜውም በላይ ሰላም: ልማትና ዴሞክራሲ ያስፈልጋታል ብለዋል።

የኢትዮጵያ ታሪክ ተቆጥረው በማያልቁ በብዙ ኩነቶች የደመቀ ስለሆነ፣ አሁን ግን ያለፈው እንዳለፈ ተቆጥሮ አውዳሚ ከሆኑ አስተሳሰቦችና ድርጊቶች ውስጥ መውጣት የግድ ነው፡፡

አገርንና ሕዝብን ረስቶ የእራስ ጥቅም ላይ ብቻ ማተኮር፣ ግላዊና ቡድናዊ ፍላጎትን ከአገር ማስበለጥና የኢትዮጵያዊያንን ዘመን ተሸጋሪ የጋራ ማኅበራዊ እሴቶችን ዋጋ አልባ ማድረግ የሚጠቅመው ታሪካዊ ጠላቶቻችንን ነው፡፡

እንዲህ ዓይነት አመለካከትና ፍላጎት የሚያስገኘው ሰላም የራቃትና ደካማ ኢትዮጵያን መሻትን ስለሆነ፣ ለአገር እናስባለን የሚሉ ወገኖች በሙሉ ከኢትዮጵያ ሰላም የሚቀድም ምንም ነገር የለም በማለት በጋራ መነሳት አለባቸው፡፡

አገር ሰላም ውላ እንድታድር በዞናችን ውስጥ ያሉት ሁሉም ወረዳዎችና የከተማ አስተዳደሮች የተናጠልና የወል ኃላፊነት ሊኖራቸው ይገባል ብለዋል፡፡

በሁሉም ሥፍራ ሁሉንም ኢትዮጵያዊያን በእኩልነት ማየት፣ አንዱን ከሌላው አለማበላለጥ፣ በሥራም ሆነ በተለያዩ ግንኙነቶች ሊገኙ የሚገቡ ጥቅሞች ከአድልኦ የፀዱ እንዲሆኑ መትጋት፣ ማንነትን ተገን በማድረግ የሚፈጸሙ መጠቃቀሞችና መጠቃቃቶች እንዳይኖሩ መከላከልና የመሳሰሉት በኃላፊነት ሲከናወኑ ብልፅግናችን ማረጋገጥ እንችላለንም ነው ያሉት፡፡

በተለያዩ የአገሪቱ ክፍሎች አንዱን ባለቤት ሌላውን መጤ በማድረግ ኢትዮጵያዊነትን የሚሸረሽሩ ከፋፋይ ድርጊቶች መወገድ አለባቸው ብለዋል፡፡

የአንድን አገር ሕዝብ በማንነትና በእምነት በመከፋፈል አገር አልባ ለማድረግ የተሠሩ ደባዎች በሙሉ ማክሸፍና አደብ ሊናስይዛቸው መስዋዕት መሆን ይገባል ብለዋል፡፡

ሕዝቡ በአገሩ ደስተኛ ሆኖ በሰላም መንቀሳቀስና ዴሞክራሲያዊ መብቱ የተጠበቀ እንድሆኑ ሁሉም ዜጋ የበበኩሉን ኃላፊነት ሊወጣና ለሚፈልገው መስዋዕትነት ሁሉ ዝግጁ መሆን አለበት።

ኢትዮጵያ ዘመን ተሸጋሪ የሆኑና በተለያዩ ማኅበረሰቦች ውስጥ ውጤታማ የሆኑ የግጭት አፈታትና የሽምግልና ሥርዓቶች ያላት ሀገር ናት፡፡ እነዚህን የሚያኮሩና ለሌላ የሚተርፉ ማኅበራዊ እሴቶችና ትሩፋቶች ይዞ አገርን ችግር ውስጥ መጣል ሊቆም ይገባል ሲሉም አሳስበዋል፡፡

ኢትዮጵያዊያን ልዩነቶቻቸውን በአግባቡ እያስተናገዱ በአንድነት አገራቸውን መገንባት እንደሚችሉ በተግባር ማሳየታችንን ማስቀጠል አለብን ብለዋል በመልዕክታቸው፡፡

በታሪክ ጠባሳዎች ላይ ብቻ በማተኮር እርስ በርስ ለመተናነቅ ከማድባት ይልቅ፣ ያለፉትን ስህተቶች በጋራ እያረሙና እያስተካከሉ በወንድማማችነትና በእህትማማችነት አብረው መኖር አያቅተንም፡፡

ኢትዮጵያዊያን በብሔር፣ በሃይማኖት፣ በባህል፣ በቋንቋና በሌሎች ጉዳዮች የየራሳቸው የሆኑ መገለጫዎች ቢኖሩዋቸውም፣ ሁሉንም በእኩልነት የምታስተናግድ ኅብረ ብሔራዊት አገር በመሆኗ ይህንኑ እንገነባ ሲሉ ጥሪ አስተላልፈዋል፡፡

ለዘመናት የብሔርና የእምነት ልዩነት ሳይገድባቸው ተጋብተውና ተዋልደው ታላላቅ ማኅበራዊ እሴቶችን ያፈሩ ኢትዮጵያዊያን፣ ለጠላት በተገዙ የግጭት ነጋዴዎች መበለጥ የለባቸውም፡፡

የአንድ ወገን የበላይነት የተጫጫናቸውን አጓጉልና ኋላቀር ትርክቶች በማስወገድ፣ የወደፊቱን የጋራ ብሩህ ሕይወት አመላካች ጉዳዮች ላይ ማተኮር አለብን፡፡

በታሪክ አንፀባራቂ የሚባሉ ክንውኖችን ብቻ ሳይሆን አስከፊ የሚባሉት ፈተናዎችንም በመቀበልና ፈተናውንም ወደ ዕድል በመቀየር ፣ የወደፊቷ ኢትዮጵያን በጋራ ሊገነቡ የሚያስችሉ የመሠረት ድንጋዮችን ማኖር ተገቢ ነው ብለዋል፡፡

ከኢትዮጵያ ሰላም የሚቀድም ነገር የለምና፡፡ ለሀገራችን ሰላም : ልማትና ዴሞክራሲ የምጠብቅብን መስዋዕነት ሁሉ ለመክፈል ፓርቲው ዝግጁ መሆኑን ተናግረዋል።

ዛሬ የመስዋዕትነት ቀን ስከብር የትላንቱን ብቻ ሳይሆን ለዛሬና ለነገው መስዋዕትነት ለመክፈል ዝግጁ መሆን አለብንም ነው ያሉት ።

ኢትዮጵያ በልጆቿ ተከብራና ተፈርታ ለዘላለም ትኑር!!

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Back To Top