ለሁለት ተከታታይ ቀናት ሲካሄድ የቆየው የደቡብ ቤንች ወረዳ ም/ቤት 5ኛ ዙር 33ኛ መደበኛ ጉባኤ የተለያዩ የወረዳውን የካብኔ አባላት ሹመት በማፅደቅ ተጠናቅቋል ።

ለሁለት ተከታታይ ቀናት ሲካሄድ የቆየው የደቡብ ቤንች ወረዳ ም/ቤት 5ኛ ዙር 33ኛ መደበኛ ጉባኤ የተለያዩ የወረዳውን የካብኔ አባላት ሹመት በማፅደቅ ተጠናቅቋል ።

በሁለት ቀናት የጉባኤው ቆይታም ም/ቤቱ የአስፈጻሚዎችን፣ የፍ/ቤቱን እና የምክር ቤቱን
የ2015ዓ.ም ሪፖርት እና የ2016ዓ.ም እቅድ ገምግሞ አጽድቋል ።

ምክር ቤቱ የወረዳውን ካቢኔ ሹመት ፕሮፖዛል በወረዳው ዋና አስተዳዳሪ አቶ ወልዱ ባጪ አማካይነት ቀርቦ ም/ቤቱ የካቢኔ አባላት ላይ አስተያየት ከሰጠበት በኋሏ አፅድቋል በዚሁ መሰረት:-
1ኛ. አቶ ብርሃኑ ተስፋዬ የደቡብ ቤንች ወረዳ ግብርና ጽ/ቤት ሀላፊ
2ኛ.አቶ ወንድሙ ሰውነት ሰላም ፣ጸጥታና ሚሊሻ ጽ/ቤት ሀላፊ
3ኛ.ወ/ሮ ሸዋዬ ጉደማ የሴቶች፣ህጻናት ፣ወጣቶችና ጽ/ቤት ሀላፊ
4ኛ.ወ/ሪት ታደለች ጋይድ ፐብሊክ የሰርቪስ ጽ/ቤት ሀላፊ
5ኛ.አቶ ዳንኤል ዘለቀ ንግድ ፣ክህሎትእና ኢንተርፕራይዝ ጽ/ቤት ሀላፊ
6ኛ.አቶ በረከት አይበራ በህል፣ቱሪዝምና ስፖርት ጽ/ቤት ሀላፊ
7ኛ.አቶ ዳንኤል ወዳጆ የከተማ እና ቤቶች ልማት ጽ/ቤት ሀላፊእንዲሆኑ ም/ቤቱ በሙሉ ድምጽ ያጸደቀ ሲሆን የካቢኔ አባላቱም ቃለ-መሀላ ፈጽመዋል።

ምክር ቤቱም በተጨማሪ የወረዳውን የ2016ዓ.ም በጀት 339 ሚሊዮን 483 ሺ2 መቶ5 ብር ማፅደቁን ከወረዳው መንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Back To Top