ህገ- ወጥ የከተማ መሬት ወረራን በመከላከል እና በማስተካከል ከተሞች ለነዋሪዎች ምቹ እና ለቱሪዝም ሳቢ እንዲሆኑ መስራት እንደሚገባ ተገለፀ።

ህገ- ወጥ የከተማ መሬት ወረራን በመከላከል እና በማስተካከል ከተሞች ለነዋሪዎች ምቹ እና ለቱሪዝም ሳቢ እንዲሆኑ መስራት እንደሚገባ ተገለፀ።

ሚዛን አማን ጳጉሜ 2/2015 ዓ.ም የቤንች ሸኮ ዞን ከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን መምሪያ ያለፍቃድ የተያዘ የከተማ ይዞታ ማስተካከልና መከላከል ደንብ ቁጥር 012/2015 እና የ2016 ዕቅድ ዝግጅት ላይ ያተኮረ የንቅናቄ መድረክ በሲዝ ከተማ እየተካሄደ ነው።

የዕለቱ የክብር ዕንግዳ እና የቤንች ሸኮ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ቀበሌ መንገሻ እንደገለፁት ህገ-ወጥ የከተማ መሬት ላይ የቅድመ መከላከል ሥራ ላይ በይበልጥ በማተኮር በከተሞች ፕላን ጥሰት ላይ የሚስተዋሉ ችግሮችን መቅረፍ ይገባል ብለዋል።

ህገ- ወጥ የመሬት ወረራን ለመከላከል የከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ከፍትህ መዋቅር ጋር ተቀናጅተው ሊሰሩ እንደሚገባ ዋና አስተዳዳሪው ተናግረዋል።

የኮንስትራክሽን ቁጥጥር ሥራን በማጠናከር ግለሰቦችም ሆኑ መንግስትን አላስፈላጊ የሆነ ጉዳት ውስጥ እንዳያስገባ ከጅምሩ የቁጥጥር ተግባሩ መጠናከር ይገባዋል ሲሉ የዞኑ አስተዳዳሪ ተናግረዋል ።

የቤንች ሸኮ ዞን ከተማ ልማትና ኮንስትራክሽል መምሪያ ኃላፊ አቶ ዘለቀ ንጉሴ እንደገለፁት ከተሞች ላይ ዘላቂነትና ቀጣይነት ያለውን የከተማ ዕድገት ለማስመዝገብ ከከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ፖሊሲዎች እና የልማት ፓኬጆችን ከነዋሪው ህዝብ ቁጥር ተጠቃሚነት ጋር በማስተሳሰር እየተሰራ መሆኑን ገልፀዋል ።

በመሬት ዘርፍ፣ በከተሞች አደረጃጀት ፕላን ዝግጅት፣ በማስፈፀም አቅም ግንባታ ላይ መመሪያው ጠብቆ ከመስራት እና መመሪያው ከማስከበር አንፃር ክፍተት እንዳለ አቶ ዘለቀ ጠቁመዋል ።

አሁን ካለው የከተሞች ፈጣን ዕድገት አንፃር ህገ ወጥ የመሬት ወረራ እየተበራከተ በመሆኑ በደንቡ ላይ የጋራ ግንዛቤ በመያዝ በ2016 በጀት ዓመት የተሻለ ሥራ መስራት ይጠበቅብናል ሲሉ አቶ ዘለቀ ንጉሴ ተናግረዋል።

የሲዝ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አቶ ሽፈራው ኮምት በእንኳን ደህና መጣችሁ ንግግራቸው በዞኑ ያሉ ከተሞችን ለነዋሪዎች ሆነ ለቱሪስት መዳረሻነት ምቹ ለማድረግ እየተሰራ ያለው ሥራ በሲዝ ከተማ አስተዳደርም ዘርፈ ብዙ ሥራ መሰራቱን ጠቁመው ተሳታፊዎች በተለያዩ መሰረተ ልማቶች በለውጥ ውስጥ ወዳለችው ሲዝ ከተማ እንኳን ደህና መጣችሁ ብለዋል።

ያለፍቃድ የተያዘ የከተማ ይዞታ ማስተካከልና መከላከል ደንብ ቁጥር 012/2015 ፣የ2015 የተግባር አፈፃፀም ን መነሻ በማድረግ የ2016 ዕቅድ እየቀረበ ይገኛል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Back To Top